Daily Weather Report August 15

Weather Summary for previous day

Aug. 14, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ፣ ድቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ጌዴኦ፣ ሀዋሳ፣ አሶሳ፣ አኙዋክ፣ ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ፣ ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በቅዳሜ ገበያ 58.4፣ በጊዳ አያና 47.1 እና በሾላ ገበያ 40.5 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል ድሬዳዋ፣ ጎዴ፣ በመንደር11፣ ፉኝዶ እና በጋምቤላ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.6-38.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Cloud cover was observed over the western, northern, northwestern, northeastern, eastern, central, southern, and southwestern parts of our country during the previous day. In association with this, light to moderate rainfall was recorded over Addis Ababa, Dire Dawa, Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, North, East, Southwest, and West Shewa, Bench Sheko, Dawuro, Gedeo, Hawassa, Assosa, Agnuwak, West, Central, North and South Gondar, North and South Wollo, West and East Gojjam, North Shoa, Silte, Gurage, and Southeast Tigray zones. Heavy rainfall of 58.4, 47.1 and 40.5 mm was recorded at Kidame Gebeya, Gida Ayana, and Shola Gebeya respectively. On the other hand, daily maximum temperatures of 35.6–38.5°C were recorded at Dire Dawa, Gode, Mender-11, Fugnido, and Gambella.

Weather Forecast for next day

Aug. 16, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ ምስራቅ እና በደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ጥንካሬ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ እና ጌዴኦ ዞኖች እንዲሁም የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ጅማ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ32 እስከ 41 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, Weather conditions favorable for Kiremt rainfall will continue across much of the northern, western, southwestern, central, eastern, and southern parts of the country, with generally similar intensity. As a result, much areas of West, Central, Northwest, Southeast, South, and East zones in Tigray region; West, North, South, and Central Gondar; West and East Gojjam; Awi; North and South Wollo; Oromo Special Zone; North Shewa; and Waghemra zones in Amhara region; Metekel, Assosa, Mao-Komo, and Kamashi zones in Benishangul-Gumuz; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, West and East Wollega, Horo Guduru Wollega, Kelem Wollega, Southwest Shewa, East Shewa, North Shewa, West Shewa, Guji, West Guji, Bale, East Bale, West and East Harerge, Arsi and West Arsi zones of Oromia region; Addis Ababa; Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Konta, West Omo, and Dawro zones of Southwest Ethiopia region; Angwak, Itang, Nuer, and Majang zones of Gambella region; Gurage, East Gurage, Mareko special woreda, Silte, Yem special woreda, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones of Central Ethiopia region; Wolaita, Gamo, and Gedeo zones, together with all zones of Sidama region are expected to receive light to moderate rainfall of (1–29 mm). In addition, South Gondar, West and East Gojjam, Jimma, and West Shoa zones are likely to receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours.

On the other hand, maximum daytime temperatures of 32°C to 41°C are expected to be recorded in Semera, Elidar, Fugnido, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Dalifage, Awash Arba, and Gode.