Daily Weather Report August 14
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምዕራብና አርሲ፣ ባሌ፣ ወላይታ፣ ጌዴኦ ፣ መተከል፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ፣ ማዕከላዊ እና በምስራቅ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤በጎብየሬ 45.6 ፣ ሐራ 30.0፣ ጎብዬ 36.3 እና አሸሬ 32.0 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ ፉኝዶ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-40.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the western, northern, northwestern, northeastern, eastern, central and southwestern regions of our country. In connection with this, light to moderate rainfall was recorded in Ilubabor, Horo Guduru, Buno Bedele, Kelem, East and West Welga, North, East, Southwestern and West Shewa, West Hararge, West and Arsi, Bale, Wolaita, Gedeo, Metekel, South and Central Gondar, Awi Zone, Waghema, West and East Gojam, South Wollo, North Shewa, Silte, Gurage, Central and Eastern Tigray zones. Heavy rainfall was recorded in Gobyere 45.6, Hara 30.0, Gobye 36.3 and Ashere 32.0 mm. On the other hand, the highest daily temperatures were recorded in Samara, Dalifage, Awash Arba, Melka Jebdu, Dire Dawa, Fugendo and Gode, ranging from 35.0-40.0°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው፣ ምስራቅ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረዉ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዴኦ ዞን እና የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ጅማ እና ምዕራብ አርሲ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ32 እስከ 41 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow Weather conditions conducive to the occurrence of kiremet rains will continue to intensify over the southwest, west, north, northeast, central, east and south of the country. In this regard, the west, central, northwest, southeast, south and east zones of Tigray region; the west, north, south and central Gondar, west and east Gojam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghemra zones of Benishangul Gumuz region; From the Oromia Region, the Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, West and East Welga, Horogudru Welga, Kelem Welga, Southwest, East, North and West Shewa, Guji, Bale and East Bale, West and East Hararge, Arsi and West Arsi zones; Addis Ababa; from the Southwestern Ethiopia Region, the Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones; from the Gambella Region, the Anwak, Itang, Nuer and Majang zones; from the Central Ethiopia Region, the Gurage, East Gurage, Marekko Special District, Silte, Me Special District, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; All zones of the Southern Ethiopia Region, including Wolaita and Gedeo Zones and Sidama Region, will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in many areas. Additionally, our forecast data indicates that West and East Gojam, South Gondar, Buno Bedele, East Wellega, Horogudru Wellega, Jimma and West Arsi will receive heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, in Semera, Elidar, Fugendo, Melka Jebdu, Mahoni, Diredawa, Aisha, Dalifage, Awash Arba, Gode and Kebridehar, the maximum temperature of the day will be recorded between 32 and 41 degrees Celsius.