Daily Weather Report August 13
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ጌዴኦ፣ ሀዋሳ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ማጃንግ፣ ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ እና ማዕከላዊ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ ሂርና 98.3 ፣ ደብረ ታቦር 63.1 ፣ ንፋስ መውጫ 32.1 ፣ ሞጣ 49.0 ፣ ዳንግላ 74.0 ፣ ቻግኒ 30.0 ፣ ካችስ 377.2 ፣ ነቀምቴ 89.3 ፣ አዳማ 60.5 ፣ መተሐራ 47.8 ፣ ኑራ ኤራ 43.3 ፣ ባቱ 37.8 ፣ አዳሚ ቱሉ 37.3 ፣ ቅዳሜ ገበያ 46.6 ፣ ቁልቢ 37.5 ፣ ጉጉፍቱ 33.8 ፣ ደብረ ሲና 63.5 ፣ ጊናገር 48.9 ፣ ሮቢት 35.0 ፣ ሰቆጣ 54.3፣ አንኮበር 41.0፣ጎብዬሬ 33.5 ፣ አዲስ ዘመን 36.2 ፣ ኮረም 37.6 ፣ ቀርሳ 35.4 ፣ አሳሳ 43.5 እና ድሬ ሸከና ሁሴን 36.3 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ መሆኒ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ ዳሊፋጌ፣ ቀብሪደሃር፣አዋሻ አርበ፣ ጎዴ፣ ድሬ ሸከና ሁሴን ፣መተሐራ እና ፉኝዶ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.0-42.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud cover was present over the western, northern, northwestern, northeastern, eastern, central, and southwestern parts of the country. In connection with this, Addis Ababa, Dire Dawa, and the zones of Jimma, Illubabor, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, North, East, Southwest, and West Shewa, West and East Hararghe, Bale, Arsi and West Arsi, Bench Sheko, Dawro, Gedeo, Hawassa, Assosa, Metekel, Majang, West, Central, North, and South Gondar, Wag Hemra, South Wollo, West and East Gojjam, North Shewa, Silte, Gurage, and South, Southeast, East, and Central Tigray received light to moderate rainfall. Heavy rainfall was recorded in Hirna 98.3, Debre Tabor 63.1, Nefas Mewcha 32.1, Motta 49.0, Dangila 74.0, Chagni 30.0, Kachis 37.2, Nekemte 89.3, Adama 60.5, Metehara 47.8, Nura Era 43.3, Batu 37.8, Adami Tulu 37.3, Kidame Gebeya 46.6, Kulubi 37.5, Guguftu 33.8, Debre Sina 63.5, Ginager 48.9, Robit 35.0, Sekota 54.3, Ankober 41.0, Gobyere 33.5, Addis Zemen 36.2, Korem 37.6, Kersa 35.4, Asasa 43.5, and Dire Sheik Hussein 36.3 mm. On the other hand, maximum daily temperatures ranging from 35.0°C to 39.0°C were recorded in Semera, Mehoni, Melka Jebdu, Dire Dawa, Dalifage, Kebridehar, Awash Arba, Gode, Dire Sheik Hussein, Metehara, and Fugnido.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የምዕራብ አጋማሽ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው፣ ምስራቅ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ እና የተስፋፋ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ከፋ ዞኖች፤ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ወረዳ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ወረዳ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዴኦ ዞን እና የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ እና አዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ32 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, strong and widespread cloud cover will persist over the western half, northeastern, central, eastern, and southern parts of the country. In connection with this, many places in the West, Central, Northwest, Southeast, South, and East zones of the Tigray region; the West, North, South, and Central Gondar, West and East Gojjam, Awi zone, North and South Wollo, Oromia Special zone, North Shewa, and Wag Hemra zones of the Amhara region; the Metekel, Assosa, Mao Komo, and Kamashi zones of the Benishangul Gumuz region; the Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, West and East Wollega, Horo Guduru Wollega, Kelem Wollega, Southwest, East, North, and West Shewa, Guji, Bale and East Bale, West and East Hararghe, Arsi, and West Arsi zones of the Oromia region; Addis Ababa; the Sheka, Bench Sheko, and Keffa zones of the Southwest Ethiopia Peoples' region; the Anywaa, Itang, Nuer, and Majang zones of the Gambella region; the Gurage, East Gurage, Mareko special wereda, Silte, Yem special wereda, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones of the Central Ethiopia region; the Wolayita and Gedeo zones of the South Ethiopia region; and all zones of the Sidama region will receive light to moderate rainfall (1–29 mm). Additionally, East and West Gojjam, West and East Wollega, Kelem Wollega, Metekel, Assosa, as well as North and West Shewa will receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. On the other hand, maximum daily temperatures ranging from 32°C to 40°C will be recorded in Semera, Elidar, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Dalifage, Awash Arba, Gode, and Kebridehar.