Daily Weather Report August 11

Weather Summary for previous day

Aug. 10, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምዕራብና አርሲ፣ ባሌ፣ ወላይታ፣ ጌዴኦ ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ እና ደቡብ በምስራቅ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ደምቢ ዶሎ 40.3 እና ጊምቢ38.7 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ገዋኔ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ መተማ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-39.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud cover was present over the western, northern, northwestern, northeastern, eastern, central, and southwestern parts of the country. In connection with this, Addis Ababa and the zones of Ilubabor, Horo Guduru, Buno Bedele, Kelem, East and West Wollega, North, East, Southwest, and West Shewa, West Harerge, West Arsi and Arsi, Bale, Wolayta, Gedeo, Assosa, Metekel, South and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, West and East Gojjam, South Wollo, North Shewa, Silte, Gurage, and South and East Tigray received light to moderate rainfall. Heavy rainfall was recorded in Dembi Dolo, 40.3 and Gimbi, 38.7 mm. On the other hand, maximum daily temperatures ranging from 35.0°C to 39.4°C were recorded in Semera, Gewane, Dalifage, Awash Arba, Melka Jebdu, Mehoni, Metema, Dire Dawa, Metehara, and Gode.

Weather Forecast for next day

Aug. 12, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው፣ ምስራቅ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረዉ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዴኦ ዞን እና የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ምስራቅ ጎጃም፣ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ጅማ፣መተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ምዕራብ አርሲ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ32 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, weather conditions favorable for Kiremt rainfall will continue to strengthen further over the southwestern, western, northern, northeastern, central, eastern, and southern parts of the country. In connection with this, many places in the West, Central, Northwest, Southeast, South, and East zones of the Tigray region; the West, North, South, and Central Gondar, West and East Gojjam, Awi zone, North and South Wollo, Oromia Special zone, North Shewa, and Wag Hemra zones of the Amhara region; the Metekel, Assosa, Mao Komo, and Kamashi zones of the Benishangul Gumuz region; the Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, West and East Wollega, Horo Guduru Wollega, Kelem Wollega, Southwest, East, North, and West Shewa, Guji, Bale and East Bale, West and East Hararghe, Arsi, and West Arsi zones of the Oromia region; Addis Ababa; the Sheka, Bench Sheko, Keffa, Konta, West Omo, and Dawro zones of the Southwest Ethiopia; the Anywaa, Itang, Nuer, and Majang zones of the Gambella region; the Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones of the Central Ethiopia region; the Wolayita and Gedeo zones of the South Ethiopia region; and all zones of the Sidama region will receive light to moderate rainfall (1–29 mm). Additionally, East Gojjam, Buno Bedelle, West and East Wollega, Horo Guduru Wollega, Kelem Wollega, Jimma, Metekel, Assosa, Mao Komo, and West Arsi will receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. On the other hand, maximum daily temperatures ranging from 32°C to 40°C will be recorded in Semera, Elidar, Pinyudo, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dalifage, Awash Arba, Gode, and Kebridehar.