Daily Weather Report August 10
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ሀዋሳ፣ መተከል፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ፣ ጉራጌ፣ ማዕከላዊ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ ቢላምቢሎ 52.6፣ጅማ 50.7፣ ደባርቅ 37.4፣ ደብረ ታቦር 34.5፣ ካቺስ 31.0፣ ፣ ጭራ 31.8፣ አጋርፋ 32.6፣ ሀሮ 50.0፣ ኮረም 34.5፣ጉዶበርት 30.0፣ ሮቢት 31.4፣ ሰቆጣ 35.8፣ ቁሉቢ 37.4 እና ሂርና 30.2 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል ሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.6-40.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the western, northern, northwestern, northeastern, eastern, central, and southwestern parts of the country. In connection with this, Addis Ababa, Harar, and the zones of Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, West and East Wollega, North, East, Southwest, and West Shewa, East and West Harerge, West Arsi, Bale and East Bale, Hawassa, Metekel, North, South, and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, West and East Gojjam, North and South Wollo, Oromia Special zone, North Shewa, Gurage, Central and East Tigray received light to moderate rainfall. Heavy rainfall was recorded in Bilambilo 52.6, Jimma 50.7, Haro 50.0, Debark 37.4, Kulubi 37.4, Sekota 35.8, Debre Tabor 34.5, Korem 34.5, Agarffa 32.6, Chira 31.8, Robit 31.4, Kachis 31.0, Hirna 30.2, and Gundoberet 30.0 mm. On the other hand, maximum daily temperatures ranging from 36.6°C to 40.4°C were recorded in Semera, Gewane, Awash Arba, and Kebridahar.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሰሜን ምዕራብ፤ በምዕራብ ፣በሰሜን ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራና የተስፋፋ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ዞን እና የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ ትግራይ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ጅማ፣ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣አዲስ አበባ እና ምዕራብ አርሲ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, strong and widespread cloud cover will persist over the northwestern, western, northern, central, northeastern, southern, and southwestern parts of the country that benefit from Kiremt rainfall. In connection with this, many places in the West, Central, Northwest, Southeast, South, and East zones of the Tigray region; the West, North, South, and Central Gondar, West and East Gojjam, Awi zone, North and South Wollo, Oromia Special zone, North Shewa, and Wag Hemra zones of the Amhara region; the Metekel, Assosa, Mao Komo, and Kamashi zones of the Benishangul Gumuz region; the Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, West and East Wollega, Horo Guduru Wollega, Kelem Wollega, Southwest, East, North, and West Shewa, Guji, Bale and East Bale, West Harerge, Arsi, and West Arsi zones of the Oromia region; Addis Ababa; the Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo, and Dawro zones of the Southwest Ethiopia Peoples' region; the Agnuwak, Itang, Nuer, and Majang zones of the Gambella region; the Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones of the Central Ethiopia region; the Gedeo zone of the South Ethiopia region; and all zones of the Sidama region will receive light to moderate rainfall (1–29 mm). Additionally, Central, Northwest, and East Tigray; North, South, and Central Gondar; West and East Gojjam; Jimma; East Wollega; Horo Guduru Wollega; Southwest, East, North, and West Shewa; Addis Ababa; and West Arsi will receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. On the other hand, maximum daily temperatures ranging from 35°C to 40°C will be recorded in Semera, Elidar, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dalifage, Awash Arba, Gode, and Kebridehar.