Daily Weather Report August 08
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ዳውሮ፣ አሶሳ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ጉራጌ፣ ምስራቅ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ጨፋ 34.4 እና ደብረ ታቦር 30.4 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል ፉኝዶ እና ድሬዳዋ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.8-37.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud cover was present over the western, northern, northwestern, northeastern, eastern, central, and southwestern parts of the country. In connection with this, Addis Ababa; Dire Dawa; and the zones of Jimma, Illubabor, Horo Guduru Wollega, Kelem Wollega, West and East Wollega, North, East, Southwest, and West Shewa, East and West Hararghe, Arsi, Sheka, Bench Sheko, Keffa, Dawro, Assosa, West, North, South, and Central Gondar, Awi, Wag Hemra, West and East Gojjam, North and South Wollo, North Shewa, Gurage, and East Tigray received light to moderate rainfall. Heavy rainfall was recorded in Cheffa 34.4 and Debre Tabor 30.4 mm. On the other hand, high daily temperatures ranging from 36.8°C to 37.0°C were recorded in Pinyudo and Dire Dawa.\
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሀኔታ ክስተቶች በምዕራብ አጋማሸ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ደቡብ ምዕራብ ፣በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ፋንቲ፣ እና አዉሲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ እና የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ደቡብና ጎንደር፣ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ምስራቅ ወለጋ፣አርሲ እና ምዕራብ አርሲ እና የም ልዩ ዞን በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ጋሞ፣ ቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ኖጎብ እና ቆራሔ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, weather conditions favorable for Kiremt rainfall will continue to strengthen over the western half, northeastern, southwestern, southern, central, and eastern parts of the country. In connection with this, many places in the West, Central, Northwest, Southeast, South, and East zones of the Tigray region; the West, North, South, and Central Gondar, West and East Gojjam, Awi zone, North and South Wollo, Oromia Special zone, North Shewa, and Wag Hemra zones of the Amhara region; the Kilbeti, Fanti, and Awusi zones of the Afar region; the Metekel, Assosa, Mao Komo, and Kamashi zones of the Benishangul Gumuz region; the Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, West and East Wollega, Horo Guduru Wollega, Kelem Wollega, Southwest, East, North, and West Shewa, Guji, Bale and East Bale, West and East Hararghe, Arsi, and West Arsi zones of the Oromia region; Addis Ababa; Harar; the Sheka, Bench Sheko, Keffa, Konta, West Omo, and Dawro zones of the Southwest Ethiopia Peoples' region; the Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones of the Central Ethiopia region; the Wolayita, Gamo, Gofa, and Gedeo zones of the South Ethiopia region; and all zones of the Sidama region will receive light to moderate rainfall (1–29 mm). Additionally, South Gondar, East Gojjam, North Shewa, East Wollega, Arsi, West Arsi, and the Yem special zone are expected to receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. On the other hand, Gamo, Borena, West Guji, and the Dawa, Liben, Afder, Shabelle, Nogob, and Korahe zones of the Somali region will receive light rainfall in a few places. Meanwhile, high daily temperatures ranging from 35°C to 40°C will be recorded in Semera, Elidar, Pinyudo, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dalifage, Awash Arba, Gode, and Kebridehar.