Daily Weather Report Agust 07
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ አኝዋክ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ አውሲ፣ ፋፈን፣ ስልጤ እና ጉራጌ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በማንኩሽ 33.0፣ በአርጆ 36.2፣ በፓዌ 37.5፣ በጋሸና 46.9፣ በሀሮ 40.2 እና በዴኔባ 30.8 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ጨፋ፣ ፉኝዶ፣ አዋሽ አርባ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መተማ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-42.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in the western, northern, northwestern, northeastern, central, and southern parts of our country, there was cloud cover and wind. In addition to this, in Addis Ababa, Dire Dawa, Jimma, Ilubabor, Horogudru, Buno Bedelle, western and eastern Wellega, the north, East, South West, and West Shoa, Western and Eastern Hararge, Arsi, Bench Shekko, Dawuro, Agnuak, Asosa, Metekel, West, North, South and Centeral Gondar, Awi zone, Waghemra, West and East Gojjam, North and South Wallo, Awusi, Fafan, Silte, and Gurage zones, moderate light to moderate rainfall recorded. In Mankush 33.0 mm; in Arjo 36.2 mm, in Pawe 37.5, in Gashena 46.9, in Haro 40.2, and in Deneba 30.8 mm of heavy rainfall were recorded. On the other hand, day time maximum temperatures, with Semera, Chefa, Fugnedo, Awash Arba, Melka Jebdu, Metema, Dire Dawa, Metahara, and Kebri Dehar 35.0 to 42.0°C recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን ወሎ፣ ምስራቅ ትግራይ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ መተከል፣ ጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ እና ጅማ ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
The Kiremt rainfall bearing weather systems will continue to more intensify over the northern, western, northwestern, northeastern, eastern, southwestern, and central parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem Wollega, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale, West and East Hararghe zones of the Oromia region; Addis Ababa; Dire Dawa; Harari; West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, West and East Gojjam, North and South Wollo, the Oromo special zone, and North Shoa zones of Amhara region; West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones in Tigray region; Agnuwak, Itang, Nuer, and Majang zones of the Gambella region; Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao-Komo zones in Benishangul-Gumuz region; Awsi, Kilbeti, Gabi, and Hari zones in the Afar region; Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Konta, West Omo and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; all zones of the Sidama region; and Wolaita, Gamo Gofa, and Gedeo zones in the South Ethiopia region. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected in West Gojjam, Awi zone, North Wallo, East Tigray, South West and West Shoa, Arsi, Metekel, Gurage, East Gurage, and Jimma zones. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40 degrees Celsius are expected to be recorded in Semera, Elidar, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifagee, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.