Daily Weather Report Agust 05
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ዳውሮ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ጉራጌ፣ ፋፈን፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአማን 48.7 ፣ በአዳማ 36.3 እና በአዳሚ ቱሉ 31.2 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ገዋኔ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ አዋሽ አርባ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መተማ፣ መተሐራ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-41.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in the western, northern, northwestern, northeastern, central, and southern parts of our country, there was cloud cover and wind. In addition to this, in Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Jimma, Ilubabor, Horogudru, western and eastern Wellega, East, Shoa, Western and Eastern Hararge, Arsi and West Arsi, Bale, Sheka, Dawuro, Agnuak, Majang, Asosa, Metekel, North, South and Centeral Gondar, Awi zone, Waghemra, West and East Gojjam, Silte, Gurage, Hari, East, South, Central and Southeast Tigray zones, moderate light to moderate rainfall recorded. In Dabra Markos 32.0 mm, and in Fugnedo 34.2 mm of heavy rainfall were recorded. On the other hand, day time maximum temperatures, with Semera, Gewane, Dallifage, Awash Arba, Melka Jebdu, Mehoni, Fugnido, Dire Dawa, Metahara, and Gode 35. 5 to 41.4°C recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ፋንቲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ባስኬቶ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅ ወለጋ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ምዕራብ አርሲ እና ቡኖ በደሌ ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
The Kiremt rainfall bearing weather systems will continue to more intensify over the northern, western, northwestern, northeastern, eastern, southwestern, and central parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem Wollega, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Bale, West and East Hararghe zones of the Oromia region; Addis Ababa; Dire Dawa; Harari; West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, West and East Gojjam, North and South Wollo, the Oromo special zone, and North Shoa zones of Amhara region; West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones in Tigray region; Agnuwak, Itang, Nuer, and Majang zones of the Gambella region; Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao-Komo zones in Benishangul-Gumuz region; Awsi, Fanti, Kilbeti, Gabi, and Hari zones in the Afar region; Siti, and Fafan zones in the Somali region; Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Konta, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; all zones of the Sidama region; and Wolaita, and Basketo zones in the South Ethiopia region. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected in West Gondar, Awi zone, West and East Gojjam, East Wollega, Assosa, Metekel, West Arsi, and Buno Bedelle zones. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40 degrees Celsius are expected to be recorded in Semera, Elidar, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifagee, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.