Daily Weather Report Agust 04

Weather Summary for previous day

Aug. 3, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ዳውሮ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ጉራጌ፣ ፋፈን፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአማን 48.7 ፣ በአዳማ 36.3 እና በአዳሚ ቱሉ 31.2 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ገዋኔ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ አዋሽ አርባ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መተማ፣ መተሐራ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-41.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in the western, northern, northwestern, northeastern, central, and southern parts of our country, there was cloud cover and wind. In addition to this, in Addis Ababa, Dire Dawa, Jimma, Ilubabor, Horogudru, Kellem, western and eastern Wellega, the north, the east, and West Shoa, the western and Eastern Hararge, Bale, the Arsi, Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Dawuro, Asosa, Metekel, West, North, South and Centeral Gondar, Awi zone, Waghemra, South and North Wallo, West and East Gojjam, North Shoa, Gurage, Fafan, East, and SouthEast Tigray zones, moderate light to moderate rainfall recorded. In Aman 48.7 mm; in Adama 36.3 mm, and in Adami Tulu 31.2 mm of heavy rainfall were recorded. On the other hand, day time maximum temperatures, with Semera, Gewane, Melka Jebdu, Mehoni, Awash Arba, Gambella, Fugnido, Metema, Metahara, and Kebri Dehar 35. 0to 41.0°C recorded.

Weather Forecast for next day

Aug. 5, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ፋንቲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ባስኬቶ፤ ጋሞ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ እና ጅማ ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

The Kiremt rainfall bearing weather systems will continue to intensify over the northern, western, northwestern, northeastern, eastern, southwestern, and central parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem Wollega, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale, West and East Hararghe zones of the Oromia region; Dire Dawa; Harari; West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, West and East Gojjam, North and South Wollo, the Oromo special zone, and North Shoa zones of Amhara region; West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones in Tigray region; Agnuwak, Itang, Nuer, and Majang zones of the Gambella region; Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao-Komo zones in Benishangul-Gumuz region; Awsi, Fanti, Kilbeti, Gabi, and Hari zones in the Afar region; Siti, and Fafan zones in the Somali region; Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Konta, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; all zones of the Sidama region; and Wolaita, Basketo, Gamo, Gofa, and Gedeo zones in the South Ethiopia region. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected in South Gondar, East Gojjam, East, Southwest and West Shoa, East Wollega, Buno Bedelle, Gurage, East Gurage fi Jimma zones. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40 degrees Celsius are expected to be recorded in Semera, Elidar, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifagee, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.