Daily Weather Report Agust 02
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ፣ ጉራጌ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በጎንደር 41.3፣ በቡሬ 32.4፣ በጋምቤላ 35.6 እና በአዳማ 31.4 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በድሬዳዋ 37.2 እና በጎዴ 35.0 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in the western, northern, northwestern, northeastern, central, and southern parts of our country, there was cloud cover and wind. In addition to this, in Addis Ababa, Dire Dawa, Jimma, Ilubabor, Horogudru, the western and eastern lowlands, the north, the east, the western and southern lowlands, the western Hararge, Bale, the western Arsi, Gamo, Gofa, Dawuro, the western region, the north, the south, and the central border area, Awii zone, Wellega, western and eastern Gojjam, the northern and southern Wolayta, the Oromia special zones, the Northern Shoa, Gurage, and eastern Tigray zones, moderate to heavy rain was recorded from light to moderate intensity. In Gondar, 41.3 mm; in Bure, 32.4 mm; in Gambela, 35.6 mm; and in Adama, 31.4 mm of heavy rainfall were recorded. On the other hand, the northern part experienced exceptionally high temperatures, with Dire Dawa at 37.2 degrees Celsius and Gode at 35.0 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ፋንቲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ጃራር እና ፋፈን ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ባስኬቶ፤ ጋሞ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአዲስ አበባ፤ በሰሜን ወሎ፣ ቅልበቲ፣ ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ጅማ፣ ምስራቅ ሸዋ እና አርሲ ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
The Kiremt rainfall bearing weather systems will continue to intensify over the northern, western, northwestern, northeastern, eastern, southwestern, and central parts of the country for tomorrow. In association with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in most areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem Wollega, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Bale, West and East Hararghe zones of the Oromia region; Addis Ababa, Dire Dawa, and Harari; West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, West and East Gojjam, North and South Wollo, the Oromo special zone, and North Shoa zones of Amhara region; West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones in Tigray region; Agnuwak, Nuer, and Majang zones of the Gambella region; Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao-Komo zones in Benishangul-Gumuz region; Awsi, Fanti, Kilbeti, Gabi, and Hari zones in the Afar region; Siti, Jarar, and Fafan zones in the Somali region; Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Sheka, Bench Sheko, Kaffa, West Omo, Konta, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; all zones of the Sidama region; and Wolaita, South Omo, Basketo, Gamo, Gofa, and Gedeo zones in the South Ethiopia region. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected in Addis Ababa, in North Wollo, Kilbeti, South Gondar, West and East Gojjam, Jimma, East Shoa, and Arsi zones. On the other hand, the daytime maximum temperatures of 35 to 40°C are expected to be recorded in Semera, Elidar, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifagee, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.