Daily Weather Report Agust 01
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ዳውሮ፣ ሀዋሳ፣ መተከል፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ ፋፈን፣ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በደብረማርቆስ 38.3፣ በጊዳአያና 41.5፣ በጎሬ 31.0፣ በአማን 30.5፣ በሶኮሩ 32.0፣ጅማ 37.6፣ በፊቼ 43.7 እና በጋሳየ 33.2 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በድሬዳዋ፣ መንደር11፣ ፉኝዶ እና በኑራኤራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-38.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, widespread cloud cover and wind were observed across the western, northern, northwestern, northeastern, central, and southern parts of our country. In addition, in Addis Ababa; Harar; Jimma, Ilubabor, Horogudru, the eastern Wellega, the north, the east, the south-western and West Shoa, East and West Harerge, West Arsi, Sheka, Bench Sheko, Keffa, Dawuro, Hawassa, Metekel, Centeral,North and south Gondar, Awi zone,Waghemra, East and West Gojam, North and south Wallo, Oromo ethnic zone, North Shoa, Walayita, Gurage, Fafan and Eastern Tigray zones light to moderate rainfall was recorded. In Debra Markos 38.3, Gidayana 41.5, Gore 31.0, Aman 30.5, Sokoru 32.0,Jimma 37.6, Fiche 43.7 and Gasay 33.2 mm heavy rainfall Recorded. On the other hand, in Dire Dawa, Villeg11, Fugnedo and Nura Era daily maximums temperatures ranging from 35.0 to 38.4°C recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ፋንቲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ባስኬቶ፤ ጋሞ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሰሜን ወሎ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጭፍራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, weather condition that is suitable for winter is expected to occur with intensify due to atmospheric instability in the north, northwest, northern west, northeast, east, southwest, and the central parts of our country. In associated with Oromia region, Jimma, Ilubabor, Bono, Horo Guduru, Kellem, East and West Wellega, West, North, East and South West Shoa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Bale,West and East Hararghe; Addis Ababa; Dire Dawa; Harari; from Amhara region West, Centeral,North and south Gondar, Awi zone,Waghemra, East and West Gojam, North and south Wallo, Oromo ethnic zone and North Shoa zones; from the Tigray region in the northwest, north, east, central and southern areas, from the Gambela region in the Agnuak, and Majang zones; from Benishangul-Gumuz in Assosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; from Afar region in Awusi, Fanti, Kilbeti, Gabi and Hari zones; from Somalia region in Siti and Fafen zones; from central Ethiopia in Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; From the Southwestern Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Keffa, West Omo,Konta and Dawuro zones; Sidama regional zones; from the Southern Ethiopia Wolayita, South Omo, Basketo, Gamo,Gofa and Gedeo Zones in many areas from light to moderate rainfall (ranging from 1-29 millimeters) is expected. In addition, in the North Walloo, Keffa, Konta, and West Arsi zones there will be receive heavy rainfall of more than 30 millimeters within 24 hours. On the other hand, in the Semera, Elidar, Fugnedo, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Diredawa, Ayisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Chifra, Gode and Kebridahar daytime maximum temperatures ranging from 35 to 40 degrees Celsius are anticipated.