Daily Weather Report 31 May 2024

Weather Summary for previous day

May 30, 2024

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ተስተውሎባቸዋል። በመሆኑም ከአማራ ክልል አዊ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ዝናብ ነበራቸው።

Yesterday, Cloud cover was observed in the west, south west and south parts of the country yesterday. Thus, from Awi and West Gojam zones of Amhara region; Ilubabor, Buno Dele and East Wollega zones of Oromia region received light to moderate rainfall.

Weather Forecast for next day

June 1, 2024

በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ቦረና፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ፣ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ኢታንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች ፤ ከሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ፋፈን እና ጃራር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ የየም ልዩ ዞን እና ፋፈን በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

For the coming day, Cloud cover and accumulation will be continue to intensify in the North-West, West, South, Central and Eastern parts of the country . Along with this, from Amhara region the North, West, South and Central Gondar, Awi, West and East Gojam zones; From the Oromia region of Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Horo Gudruna, Kelem Wollega, Southwest and West Showa, Borena, Arsi West Arsi, Guji West Guji, Bale, West and East Hararge zones; Harar; ; Addis Ababa; from the Benshangul Gumuz region, Metekel, Asosa, Kamash, and Mao Komo zones; from Gambella region Itang, Nuer, Anuwak and Majang zones; From South West Ethiopia Region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dawuro and West Omo Zones; From the central region of Ethiopia, Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Yem special zone, Kambata and Tmbaro zones; All zones from Sidama region; From South Ethiopia region, Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Konso, Burji, Amaro, Gedeo and South Omo zones; from Somali region Fafen and Jarar zones will receive light to moderate rainfall in most of their areas. In addition, there will be heavy rainfall in few places in Jimma, East Hararge, Yem Special Zone and Fafen within 24 hours.