Daily Weather Report 30 May 2024
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በድቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው። በመሆኑም ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ እና ወላይታ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ዝናብ አግኝተዋል። በነቀምቴ እና ቴፒ ድግሞ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, better cloud coverage was observed over the west, southwest, central, and south parts of the country. Thus, from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west, and east Welega zones; from the southwest Ethiopia region, Bench Sheko zone; and the southern Ethiopia region, Gofa and Walayita zones received light to moderate rainfall. Heavy rain was recorded over Nekamte and Tepi stations.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በተለይም በምዕራብ አጋማሽ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ይበልጥ እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ቦረና፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ፣ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ኢታንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች ፤ ከሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ ኢሉባቦር እና ቡኖ በደሌ፣ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ 30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
For the coming day, favorable weather events for the formation of rain will intensify, particularly in the western half, south, central and east parts of the country. In line with this, from Amhara region north, west, south and central Gondar, Awi, west and east Gojam zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east, west, Horo Gudruna and Kelam Welega, southwest, and west Shawa, Borena, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; from Benshangul Gumuz region, Metekel, Kemashi, Asosa and Mao Komo zones; from Gambella region, Itang, Agnuwak, Nuwer and Majang zones; from south west Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dawuro and west Omo Zones; from central Ethiopia Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Kambata and Tembaro zones; all zones from Sidama region; from south Ethiopia region, Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Konso, Burji, Amaro, Gedeo and south Omo zones and Somale region Fafan zone will receive light to moderate rainfall in some places. Additionally, the Jimma, Illubabor, and Buno Bedele zones are expected to receive more than 30 mm of heavy rainfall in a few places in 24 hours.