Daily Weather Report 30 April 2024
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ መካከለኛዉ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሸፋን ነበራቸው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፣ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉድሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲ እና ቦረና ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳዉሮና ኮንታ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን፤ ከሶማሌ ክልል ጃራር ዞን፤ ሀረርና ድሬ ዳዋ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ ከባድ ዝናብ ከተመዘገበባቸው ጣብያዎች መካከል በነጆ ይጠቀሳል፡፡
Yesterday, the North East, East, South, Central, West, and South West parts of the country had strong cloud coverage in most places. Along with this, from the Tigray region east, south, and southeast zones; from the Amhara region west, central, and south Gondar; north Wolo; west and east Gojam zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Welega; North, East, and Southwest Showa; East Hararge; Guji and West Guji; Arsi and Borena zones; from the Central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadia, Kambata, and Tenbaro zones; from the Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, and Konso zones; from the Southwest Ethiopia region Dauro and Konta zones; from the from the Gambella Region Agnuwak Zone; from the Somali Region Jarar Zone; Harar and Dire Dawa recorded light to heavy rainfall. Nedjo is mentioned among the stations where heavy rain has been recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ ዞኖች እና የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ፋንቲ፣ ሀቲ፣ አዉሲ እና ጋቢ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የኢሉባቦር፤ ቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች ፤ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ አማሮ፣ ጌዴኦ፣ ቡርጂ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ሲቲ፣ ፋፈን፣ ኤረር፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ኮራሄ፣ ዶሎ እና ዳዋ ዞኖች፤ ሐረርና ድሬዳዋ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም ጅማ፣ ቦረና፤ ጉጂ፤ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፣ ደቡብ ወሎ፣ ሸካ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ኮንሶ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም በአዋሽ፤ በስምጥ ሸለቆ እና በዋቢሸበሌ ተፋሰሶችና የጎርፍ ተጋላጭ በሆኑት አካባቢዎች ማህበረሰቡ እና የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይጠቁማል፡፡
For tomorrow, numerical forecast data indicates that weather events favourable for the formation of rain will continue to strengthen. Along with this, the eastern, south eastern and southern zones of the Tigray region; from the Amhara region, South and Central Gondar, North and South Wolo, Wag hemra, Awi Zone, East and West Gojam, North Showa Zones and the Oromo Special Zone; from the Afar region of Kilbet, Fanti, Hati, Awsi and Gabi zones; Asosa, Kamash and Mao Komo zones from Benshangul Gumuz region; from Oromia region Ilubabor, Buno Bedele, Jimma, East, West, Horo Guduru and Kelem Welega, North, West, East and South West Showa, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, West and East Hararge zones; Addis Ababa; Agnuwak, Majang and Itang zones of Gambella region; from South West Ethiopia Region Sheka, Kefa, Bench Sheko, Konta, Dauro and West Omo Zones; from central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadia, Kambata and Tenbaro zones; all the zones of Sidama region; from South Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Konso, Amaro, Gedeo, Burji and South Omo zones; From Somali Region City, Fafen, Erer, Nogob, Jarar, Liben, Afder, Shebele, Korahe, Dolo and Dawa zones; Harar and Diredawa will have light to moderate rainfall at many places. Moreover, Jimma, Borena, Guji, North, East, West, and South West Showa Zones, South Wolo, Sheka, Konta, Dauro, Gamo, Gofa, Wolayta Konso, Gurage, Silte, Hadia, Kambata, and Xenbaro zones will receive heavy rainfall. Therefore, the Ethiopian Institute of Meteorology suggests that the community and concerned bodies should take necessary precautions in the Awash basin, in the Rift Valley, and in the Wabi Shebele basins and flood-prone areas.