Daily Weather Report 29May 2024

Weather Summary for previous day

May 28, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው። በመሆኑም የትግራይ ክልል ምዕራብ ዞን፤ ከአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል። በተጨማሪም በነቀምቴ፣ ጊምቢ እና አርጆ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቦባቸዋል፡፡

The previous day, cloud coverage was observed in the northwest, west, and south parts of the country. In association with, from Amhara region central Gondar, Awi and east Gojam zones; From Oromia region, Jimma, Ilubabor, west, east, and Horo Gudru Welega, west Guji zones; from Gambella region Agnuwak zone; from Southern Ethiopia region Gedeo and South Omo zones received light to moderate rainfall. Heavy rain was recorded over Nekamte, Gimbi, and Arjo stations.

Weather Forecast for next day

May 30, 2024

በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ አጋማሽ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ ዞን፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ቦረና፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች ፤ ከሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ ዞን በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ 30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡

For the coming day, favorable weather events for the formation of rain will continue to strengthen in the western half, south, southeast, central, and east parts of the country. In line with this, from the Tigray region west zone of the western, north and central zones; from Amhara region north, west, south and central Gondar, Awi, west and east Gojam zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east, west, Horo Gudruna and Kelam Welega, southwest, and west Shawa, Borena, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; from Benshangul Gumuz region, Metekel, Kemashi, Asosa and Mao Komo zones; from Gambella region, Itang, Agnuwak and Majang zones; From south west Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dawuro and west Omo Zones; from central Ethiopia Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Kambata and Tembaro zones; all zones from Sidama region; From south Ethiopia region, Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Konso, Burji, Amaro, Gedeo and south Omo zones will receive light to moderate rainfall in many places. Moreover, the Jimma zone is expected to receive more than 30 mm of heavy rainfall in a few places in 24 hours.