Daily Weather Report 28 May 2024

Weather Summary for previous day

May 27, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብ እና በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው። በመሆኑም ከአማራ ክልል ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ ፣ ምስራቅና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ባሌ፣ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በላይበር ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, they had cloud cover in the North West, Central, West and South parts of the country. Thus, from Amhara region North, South and Central Gondar, West and East Gojam zones; From Oromia region North and West Showa, East and Horo Gudru Welega, Bale, Guji zones; Addis Ababa; Basketto, Derashe, Konso, Burji, Amaro, Gedeo and South Omo zones of Southern Ethiopia region received light to moderate rainfall while Leiber recorded heavy rainfall of more than 30 mm.

Weather Forecast for next day

May 29, 2024

በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ቦረና፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል፣ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ኑዌር፣ ኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች ፤ ከሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብ ትግራይ፣ ምዕራብ ጎንደር፣ ኢሉባቦር፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሺ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ 30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡

Tomorrow there will be better cloud cover in the north-west, west, south, south-west and east areas of the country. Along with this, from Tigray region the western, north western and central zones; Amhara region North, West, South and Central Gondar, Awi, West and East Gojam zones; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Horo Gudruna, Kelem Welega, Southwest, Northwest and East Showa, Borena, Arsi West Arsi, Guji West Guji, Bale, West and East Hararge zones; Addis Ababa; from Benshangul Gumuz region: Metekel Asosa and Mao Komo zones; Gambella region Nuer, Itang, Anuwak and Majang zones; From South West Ethiopia Region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dawuro and West Omo Zones; From Central Ethiopia Gurage, Silte, Hadia, Kambata and Tembaro zones; All zones from Sidama region; From South Ethiopia region, Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Konso, Burji, Amaro, Gedeo and South Omo zones; will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, West Tigray, West Gondar, Ilubabor, Mao Komo and Kamashi zones are expected to receive more than 30 mm of heavy rainfall in a few places in 24 hours.