Daily Weather Report 27 May 2024
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በደቡብምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ከአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም እና አዊ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ከፋ ዞኖች እና ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ ከባድ ዝናብ ከተመዘገበባቸው ጣቢያዎች መካከለል ማሻ እና ነጆ ይጠቀሳሉ፡፡
Yesterday, they had cloud coverage over the northwest, southwest and west parts of the country In this regard, light to heavy amounts of rainfall were recorded from Amhara region south Gondar, west Gojjam and Awi zones, Oromia region Jimma, Ilubabor, west and east Wolega zones, Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Shekona and Kefa zones and Gambella region Anuwak zone. Among the stations where heavy rainfall was recorded were Masha and Nejo.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ ገጽታ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ቦረና፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል፣ ካማሺ፣ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ኑዌር፣ ኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ፋፈን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ ቆራሄ እና ሸበሌ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ክስተቶች ላይ በመነሳት በምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ ምዕራብ፣ ማዕከላዊና ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ከፋ፣ አሶሳ እና ካማሺ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ 30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, our forecast data indicates that weather events favorable for rainfall will have better in the northwest, west, south, southwest and eastern parts of our country. In association with this, the west, northwest, south and central zones of the Tigray region, from Amhara region north, west, south and central Gondar, Awi, west and east Gojjam zones; Oromia region Jimma, Ilubabor, Bunobedele, east, west, Horo Gudru and Kelem Wolga, southwest, north and west Shewa, Borena, Arsi west and west Arsi, Guji, west Guji, Bale, west and east Hararge Zones, Harar, Addis Ababa; Benishangul-Gumuz region Metekel, Kamashi, Assosa and Mao Como zones; Nuer, Itang, Agnuak and Majang zones of Gambella region; from the Southwest Ethiopia region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro and West Omo zones; Central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadia, Kembatana, Tembaro zones; Sidama region all zones; Wolayta, from South Ethiopia region Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Konso, Burji, Amaro, Gedeo and South Omo zones and from Somali region, Fafen, Jarrar, Erer, Korahe and Shebelle zones will receive light to moderate amounts of rainfall in most places. In addition, based on the intensifying meteorological phenomena, more than 30 mm of heavy rainfall in 24 hours will be expected in a few places of western and northwestern Tigray, west, central and north Gonder, west Gojjam, Awi, east and west Wolga, Jimma, Ilubabor, west Shewa, Kefa, Assosa and Kamashi zones.