Daily Weather Report 26 May 31
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፤ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ፣ መተከል፣ ኮንሶ፣ ጌዴኦ፣ ሸካ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በሊሙ ገነት 35.3፣ በቴፒ 30.2 እና በቴርቻ 34.8ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በመተማ 37.8 እና በጎዴ 35.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy patches over the western, northwestern, central and southern parts of our country. In connection with this, Jima, West Guji, Arsi and West Arsi, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru and East Wollega, South West and East Shewa, East Hararghe; the western, northern, southern and central parts of Gondar; western and eastern Gojjam; Awi Zone; North Shewa; Metekel; Konso; Gedeo; Sheka; Gurage; Silte; and Agnuwak zones received light to moderate rainfall. Heavy rainfall was recorded at Limu Genet (35.3 mm), Tepi (30.2 mm) and Tercha (34.8 mm). On the other hand, the day's maximum temperatures were registered at Metema, 37.8°C, and Gode, 35.2°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረሪ ክልል፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ፋፈን፣ ቆራሄ፣ ሲቲ፣ ዶሎ፣ ሸበሌ እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ እና በምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ፓዌ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, strong cloud cover and significant cloud development are expected over the western, northwestern, eastern, central, and southern parts of Ethiopia. In association with these conditions, many areas of Guji, West Guji, Borena, East Borena, Bale, East Bale, Arsi, West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, Southwest Shoa, West, East and North Shoa, and East and West Hararghe zones of Oromia Region; Addis Ababa; Harari Region; Dire Dawa; Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alle, Kore, Gardula, Burji, South Omo, and Konso Zones of South Ethiopia Region; the whole zones of Sidama Region; Dawa, Liben, Nogob, Afder, Fafan, Korahe, Siti, Dolo, Shebelle, and Jarar Zones of Somali Region; Gurage, East Gurage, Mareko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro zones of Central Ethiopia Region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and West Omo zones of Southwest Ethiopia Region; Agnuak, Majang, and Itang zones of Gambella Region; Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao-Komo zones of Benishangul-Gumuz Region; and West Gondar, South Gondar, Central Gondar, West Gojjam, East Gojjam, Awi zone, North Shoa, and South Wollo zones of Amhara Region are expected to receive light to moderate rainfall amounts ranging from 1 to 29 mm. Furthermore, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is forecast over Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, East and West Wollega, and West Shewa Zones. Meanwhile, maximum daytime temperatures ranging from 35°C to 40°C are expected to be recorded in Gambella, Fugnido, Abobo, Pawe, Semera, Elidar, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Dire Dawa, Metehara, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.