Daily Weather Report 26 May 30
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በሰሜን፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፤ ሐረር፤ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ዋግኸምራ፣ መተከል፣ ጌዴኦ፣ ከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአዴት30.0 እና በአዲስ አበባ 37.0 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ ኑራኤራ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-38.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there were clouds over the western, northwestern, eastern, northern, central and southern parts of our country. In addition, light to moderate rainfall was recorded in Jimma, Arsi and West Arsi, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, South West, West, East and North Shewa, West and East Harerge; Harar; West, North, South and Central Gondar; West and East Gojjam; Awi zone; North and South Wallo and Wag Hemra; Metekel; Gedeo; Kefa; Sheka; Bench Sheko; Gurage; Silte; and Agnuak zones. Heavy rainfall amounts were recorded at Adet with 30.0 mm and at Addis Ababa with 37.0 mm. elsewhere, in Gambella, Fugnido, Dire Dawa, Metehara, Nura Era and Gode, daytime maximum temperatures ranged from 35.0–38.4°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በሰሜን፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ በአዲስ አበባ፤ ሐረሪ ክልል፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ፋፈን፣ ቆራሄ፣ ሲቲ፣ ኤረር፣ ዶሎ፣ ሸበሌ እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ጌዴኦ፣ ወላይታ፣ ሲዳማ፣ ሀላባ እና ከምባታ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ፓዌ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, cloud cover will spread across much of the country, covering the western, northwestern, eastern, northern, central, and southern parts of the country. Along with this overcast sky, a widespread rainfall event is expected to prevail across many areas, bringing light to moderate rainfall ranging between 1 and 29 millimeters over Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kellem, East and West Wellega, Southwest, West, East and North Shoa, as well as West and East Hararghe zones of Oromia region; the Harari Region and the city of Dire Dawa; Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo, and Konso zones of South Ethiopia Region; all zones within the Sidama Region; Dawa, Liben, Nogob, Afder, Fafen, Korahe, Sitti, Erer, Dolo, Shabelle, and Jarar zone in the Somali Region; Gurage, East Gurage, Mareqo Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia Region; Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and West Omo zones of the Southwest Ethiopia Region; the Agnuak and Majang zones in the Gambella Region; Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao-Komo zones of Benishangul-Gumuz region; West, South and Central Gondar, North, West and East Gojjam, Awi Zone, North Shoa, North and South Wollo zones of the Amhara Region. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within a 24-hour period is expected over Horo Guduru and East Wollega, West Shoa, West and East Gojjam, Gedeo, Wolayita, Sidama, Halaba, and Kembata zones.