Daily Weather Report 26 May 28
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በሰሜን፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ባሌ ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፤ ሐረር፤ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ቤንች ሸኮ እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በነቀምቴ፣ ሺንዲ፣ አምቦ፣ አማን፣ አሺ እና በሶኮሩ 30.3-43.2ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አሸሬ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.4-38.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy patches over the western, northwestern, eastern, northern, central and southern parts of our country. In addition, light to moderate rainfall was recorded in West Guji, East Bale, West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, West and East Shewa, East Hararghe, Hararghe, North Gondar, West and East Gojjam, Awi zone, West Omo, Bench Sheko and Agnuak zones. Heavy rainfall of 30.3–43.2 mm was recorded in Nekemte, Shendi, Ambo, Aman, Ashi and Sokoru. On the other hand, the daytime maximum temperatures recorded in Fugnido, Melka Jebdu, Addis Zemen, Dire Dawa, Metehara, Ashere, Gode and Kebridahar ranged from 35.4 to 38.2°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በሰሜን፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ሲቲ እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ አዊ ዞን፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ እና ከምባታ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ፓዌ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, cloudy conditions are expected over the western, northwestern, eastern, northern, central, and southern parts of the country. In association with this, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Qellem, East and West Wollega, Southwest, West, East and North Shoa zones of the Oromia Region; Harari Region; Dire Dawa; Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alle, Kore, Gardula, Burji, South Omo, and Konso zones of the South Ethiopia Region; all zones of the Sidama Region; Fafan, Siti, and Jarar zones of the Somali Region; Gurage, East Gurage, Mareko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro zones of the Central Ethiopia Region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and West Omo zones of the Southwest Ethiopia Region; Agnuak, Majang, and Itang zones of the Gambella Region; Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao-Komo zones of the Benishangul-Gumuz Region; and West, North, South, and Central Gondar, North, West, and East Gojjam, Awi Zone, North and South Wollo, Oromia Special Zone, North Shoa, and Wag Hemra zones of the Amhara Region are expected to receive light to moderate rainfall amounts ranging from 1–29 mm in many places.
In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected over Jimma, Awi Zone, Buno Bedelle, Horo Guduru, East and West Wollega, Southwest and West Shoa, Gurage, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, and Kembata zones. On the other hand, daily maximum temperatures of between 35 and 40 degrees Celsius are expected to be recorded in Gambella, Fugnido, Abobo, Pawe, Semera, Elidar, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Metehara, Ayisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebri Dehar.