Daily Weather Report 26 May 26

Weather Summary for previous day

May 25, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በባሌ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ጋሞ፣ ሸካ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ቤንች ሸኮ እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በቴፒ፣ ሻምቡ፣ ነቀምቴ፣ ጎሬ እና በጅማ 33.5-57.7ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በአዲስ ዘመን፣ በጋምቤላ፣ ቀብሪደሃር፣ በመልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ ሚኤሶ፣ መሆኒ፣መቂ፣ ቡኢ፣ መተማ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-39.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, areas that benefit from the Belg season rains, as well as the western parts of our country, experienced cloud cover. In line with this Bale, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, Gamo, Sheka, East Gojjam, Bench Sheko and Agnuak zones received light to moderate rainfall; while heavy rainfall of 33.5–57.7 mm was recorded in Tepi, Shambu, Nekemte, Gore and Jimma. Elsewhere, high daytime temperatures of 35.0–39.2°C were recorded in Addis Zemen, Gambella, Kebridahar, Melka Jebdu, Dire Dawa, Meiso, Mehoni, Meki, Bui, Metema and Metehara.

Weather Forecast for next day

May 27, 2026

በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ፋፈን፣ ቆራሄ፣ ሲቲ፣ ኤረር እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ከፋ እና ሸካ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ፓዌ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, areas that benefit from the Belg season rains, as well as the western and northwestern parts of our country, will experience cloud cover. In association with this, many places within the following areas will receive light to moderate (1–29 mm) rainfall: From the Oromia region: Guji and Western Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, South West Wollega, West, East and North Shewa, West and East Hararghe zones; Harari; from the Southern Ethiopia region: Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; all zones of Sidama region; from Somali region: Dawa, Liben, Nogob, Afder, Fafan, Korahe, Siti, Erer and Jarar zones; from the Central Ethiopia region: Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, West and other special zones, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro zones; from Southern West Ethiopia region: Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela region: Agnuak, Majang and Itang zones; from Benishangul-Gumuz: Asosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones; and from Amhara region: West and East Gojjam, Awi zone, North, West, Central and South Gondar zones in many of these places light to moderate rainfall between 1 and 29 mm is expected. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected over Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, East Wollega, Keffa and Sheka zones. Elsewhere, in Gambela, Funyido, Abobo, Pawe, Semera, Elidar, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Metehara, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Gode and Kebridahar, daytime maximum temperatures are recorded between 35 and 40 degrees Celsius.