Daily Weather Report 26 May 25
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ጋሞ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ቤንች ሸኮ፣ ጉራጌ፣ አሶሳ፣ መተከል እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በአዲስ ዘመን፣ በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ፓዌ፣ አሸሬ፣ ላይ በር፣ ጨፋ፣ ቀብሪደሃር፣ በመልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ ሚኤሶ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.6-39.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, areas that benefit from the Belg season rains, as well as the western parts of our country, experienced cloud cover. In line with this light to moderate rainfall was recorded in the Ilubabor, Buno Bedelle, Wollega East and West, Gamo, Sheka, West Omo, Bench Sheko, Gurage, Asosa, Metekel and Agnuak zones. Meanwhile, the highest daytime temperatures reached between 35.6 and 39.0°C in Addis Zemen, Gambela, Funyido, Pawe, Ashere, Lay Ber, Chefa, Kebridahar, Melka Jebdu, Dire Dawa, Meiso and Metehara.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ፋፈን፣ ቆራሄ፣ ሲቲ፣ ኤረር፣ ሸበሌ እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ደቡብ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, areas that benefit from the Belg season rains, as well as the western and northwestern parts of our country, will experience cloud cover. Therefore, the following zones receive light to moderate rainfall (1–29 mm): from Oromia Region Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, South West Wollega, West and East Shewa, East and North Shewa, and West and East Hararghe zones; from Southern Ethiopia Region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alaba, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; throughout all zones of Sidama Region; from Somali Region Dawuro, Liben, Nogob, Afder, Fafan, Korahe, Siti, Erer, Shebelle and Jarar zones; from the Central Ethiopia region Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, the special zone of the South, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones; from Southwest Ethiopia Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela Region Agnuak, Nuwer, Majang and Itang zones; from Benishangul-Gumuz Assosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones; and from Amhara Region West and East Gojjam, Awi zone, South, North, West, Central and South Gondar zones. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected in the Jimma, Buno Bedelle, and East Wollega and West Shewa zones. Meanwhile, in Gambela, Funyido, Abobo, Semera, Elidar, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Metehara, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebridahar, daytime maximum temperatures are reported to reach between 35 and 40 degrees Celsius.