Daily Weather Report 26 May 24

Weather Summary for previous day

May 23, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጂንካ ፣ቴፒ ፣ አማን፣ዲላ እና በቦሬ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በድሬዳዋ፣ ጨፋ፣ ጎዴ፣ ኑራኤራ እና መተማ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-38.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, areas that benefit from the Belg season rains, as well as the western parts of our country, experienced cloud cover. In line with this,, light to moderate rains were recorded in the Jinkaa,Teppii,Amaan,Dillaa and Bore. On the other hand, in Dire Dawa, Cheffa, Gode, Nuraera and Metema the daytime maximum temperatures were recorded between 35.0 and 38.2°C.

Weather Forecast for next day

May 25, 2026

በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ፋፈን፣ ቆራሄ፣ ሸበሌ እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ደቡብ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ ዞን ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, areas that benefit from the Belg season rains, as well as the western and northwestern parts of our country, will experience cloud cover. Therefore, the following zones receive light to moderate rainfall (1–29 mm): from Oromia region Western Guji, Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, West and East Hararghe; Harar; from Southern Ethiopia region; Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alaba, Kora, Gardula, Burji, South Omo, and Konso zones; all zones of Sidama region; from Somali region Dawa, Liben, Nogob, Afder, Fafan, Korahe, Shebelle, and Jarar zones; from Central Ethiopia region Gurage, Silte, Yeem special zone, Hadiya, Halaba, Kambata and Tambaro zones; from Southwest Ethiopia region Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and West Omo zones; from Gambela region Agnuak, Nuwer, Majang, and Itang zones; from Benishangul-Gumuz Asosa, Metekel, Kamashi, and Mao Komo zones; and from Amhara region West and East Gojjam, Awi zone, South, North,West, and Central Gondar zones. In many of these places rainfall amounts will range from light to moderate (1–29 mm). On the other hand, daytime maximum temperatures between 35 and 40°C are expected in Gambela, Funyido, Abobo, Semera, Elidar, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebridahar.