Daily Weather Report 26 May 23

Weather Summary for previous day

May 22, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በምስራቅ ወለጋ፣ ቤንች ሸኮ ፣ ጉራጌ እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በድሬዳዋ፣ አቦምሳ፣ ጨፋ፣ ጎዴ፣ ኑራኤራ ፣ ሚኤሶ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-38.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were beneficial heavy rains in the highland areas and also cloudy conditions over some western parts of the country. In addition, light to moderate rains were recorded in the eastern Wollega, Bench Sheko, Gurage and Agnuak zones. On the other hand, in Dire Dawa, Abomsa, Cheffa, Gode, Nuraera, Meiso and Metehara the daytime maximum temperatures were recorded between 35.0 and 38.8°C.

Weather Forecast for next day

May 24, 2026

በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ፋፈን፣ ቆራሄ፣ ሸበሌ እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ እና ከምባታ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ደቡብ፣ ምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, areas that benefit from the Belg season rains, as well as the western and northwestern parts of our country, will experience cloud cover. Therefore, the following zones receive light to moderate rainfall (1–29 mm): from Oromia region Western Guji, Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, and East Hararghe; from Southern Ethiopia region; Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alaba, Kora, Gardula, Burji, South Omo, and Konso zones; all zones of Sidama region; from Somali region Dawa, Liben, Nogob, Afder, Fafan, Korahe, Shebelle, and Jarar zones; from Central Ethiopia region Gurage, Yeem special zone, Hadiya, Halaba, and Kambata zones; from Southwest Ethiopia region Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and West Omo zones; from Gambela region Agnuak, Nuwer, Majang, and Itang zones; from Benishangul-Gumuz Asosa, Metekel, Kamashi, and Mao Komo zones; and from Amhara region West Gojjam, Awi zone, South, West, and Central Gondar zones. In many of these places rainfall amounts will range from light to moderate (1–29 mm). On the other hand, daytime maximum temperatures between 35 and 40°C are expected in Gambela, Funyido, Abobo, Semera, Elidar, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Gode, and Kebridahar.