Daily Weather Report 26 May 22

Weather Summary for previous day

May 21, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ጎፋ፣ ጌዴኦ፣ ወላይታ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ደቡብ ኦሞ፣ ቤንች ሸኮ፣ ጉራጌ፣ አኝዋክ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በአዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ጨፋ፣ ጎዴ፣ ሚኤሶ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-40.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there was widespread scattered rain, along with cloudy conditions over parts of our country in the western and northwestern areas. In addition, light to moderate rainfall was recorded in Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, East and West Wollega, Gofa, Gedeo, Walayita, Sheka, West Omo, Bench Sheko, Gurage, Agnuak and South Omo zones. On the other hand, maximum daytime temperatures of 35.0–40.2°C were recorded in Addis Zemen, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Ayisha, Metema, Cheffa, Gode, Meiso and Metehara.

Weather Forecast for next day

May 23, 2026

በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ፋፈን፣ ዶሎ እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ እና ከምባታ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ ዞን፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, areas that benefit from the Belg season rains, as well as the western and northwestern parts of our country, will experience cloud cover. Therefore, the following zones receive light to moderate rainfall (1–29 mm): from Oromia region Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, West Arsi, Jimma, Iluababora, Bunno Bedelle, Horo Guduru, Kellem; East and West Wollega and East Harerge zones; from the Southern Ethiopia Region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kora, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; all zones of Sidama region; from Somali region Dawa, Liben, Afder, Fafan, Dolo and Jarar zones; from the Central Ethiopia region the special Yeme zone, Hadiya, Halaba and Kembata zones; from the Southwest Ethiopia region Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela region Agnuak, Nuer, Majang and Itang zones; from Benishangul-Gumuz Assosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; from Tigray region the Western zone; and from Amhara region West Gojjam, Awi zone, and West and Central Gondar zones. On the other hand, in many places in Gambela, Fugnido, Abobo, Semera, Elidar, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Gode and Kebridahar, daytime maximum temperatures are expected to be high, reaching between 35 and 40 degrees Celsius.