Daily Weather Report 26 May 21
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ጅግጅጋ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ጎፋ፣ ጌዴኦ፣ ወላይታ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ጉራጌ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ጎንደር፣ አኝዋክ እና አሶሳ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ አሸሬ፣ ፉኝዶ፣ አዳማ፣ አቦምሳ፣ ኑራኤራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-40.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there was widespread scattered rain, along with cloudy conditions over parts of our country in the western and northwestern areas. In addition, light to moderate rainfall was recorded in Jimma, Jigjiga, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, Gofa, Gedeo, Walayita, Sheka, West Omo, Gurage, western and northern Gondar, Agnuak and Asosa zones. On the other hand, maximum daytime temperatures of 35.0–40.2°C were observed in Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Kebridahar, Gode, Ashere, Funyido, Adama, Abomsa, Nura Era and Metehara.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ቆራሄ፣ ዶሎ እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ እና ከምባታ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ ዞን፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ማዕከላለዊ ጎንደር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቄለም ወለጋ ዞን ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, areas that benefit from the Belg season rains, as well as the western and northwestern parts of our country, will experience cloud cover. In addition, rain is expected in parts of Oromia including Guji and western Guji, Borena and eastern Borena, Bale, western Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, eastern and western Wollega and east Hararghe zones; from Southern Ethiopia Region in Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alaba, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; across all zones of the Sidama region; in Somali Region in Fafan, Korahe, Dolo and Jarar zones; in the central Ethiopia region in Hadiya and Kembata zones; in the Southwest Ethiopia region in Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; in Gambela in Agnuak, Nuer, Majang and Itang zones; in Benishangul-Gumuz in Assosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones; in the western zone of Tigray; and in Amhara in western Gojjam, Awi zone, and western and central Gondar zones. These areas will receive light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 mm in many places. Furthermore, the Kellem Wollega zone is expected to receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. The amount and distribution of this rain will be highly beneficial for Belg agricultural activities. Meanwhile, daytime maximum temperatures of 35 to 40 degrees Celsius have been recorded in Gambela, Funyido, Abobo, Semera, Elidar, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhanssa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Gode and Kebridahar.