Daily Weather Report 26 May 20
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ጉጂ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አሶሳ፣ ወላይታ፣ ሸካ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ አኝዋክ እና ቡርጂ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ፉኝዶ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.4-42.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were light rains in the Belg-growing areas and cloudy conditions over parts of western Ethiopia. In addition, light to moderate rain was recorded in the zones of Jimma, Guji, Illubabor, Buno Bedelle, East and west Wollega, Bale and East Bale, Asosa, Wolayta, Sheka, East Gojjam, Agnuak and Burji. Elsewhere, the daily maximum temperatures ranged from 35.4 to 42.0°C in Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Ayesha, Funyido and Metehara.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, areas that benefit from the Belg season rains, as well as the western and northwestern parts of our country, will experience cloud cover. In association with this, many places within the following areas will receive light to moderate (1–29 mm) rainfall: From the Oromia region: Gujii and West Gujii, Borena and East Borena, Bale and East Bale, West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, South West and West Shewa, and East and West Hararghe zones; Harari; from the Southern Ethiopia region the Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alaba, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; all zones of the Sidama region; from Somali region the Fafan and Jarar zones; from the Central Ethiopia region Gurage, Yeem zone, Hadiya, Kambata and Tambaro zones; from the Southern Ethiopia region Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela region Agnuak, Nuer, Majang and Itang zones; from Benishangul-Gumuz Asossa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; from Amhara region West and East Gojjam, Awi zone, West, Central and South Gondar zones many places will receive light to moderate rainfall of 1–29 mm. This amount and distribution of rain will be highly beneficial for implementing rainfed agricultural activities. Meanwhile, in Gambella, Funyido, Abobo, Semera, Elidar, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mai Hansa, Mehoni, Dire Dawa, Ayshe, Metema, Dallifage, Awash Arba, Gode and Kebridahar, daytime maximum temperatures will be high, ranging from 35 to 40 degrees Celsius.