Daily Weather Report 26 May 18
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በምዕራብ ጉጂ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ አሶሳ፣ መተከል፣ አኝዋክ እና ቡርጂ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በጊዳ አያና 59.2ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.5-39.6°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were widespread light rains in many areas, and cloudy conditions prevailed over parts of western Ethiopia. In addition, the western zones of Guji, Jimma, Iluababora, Buno Bedelle, Horo Guduru, and East Wollega, as well as East Gojjam, Asosa, Metekel, Agnuak, and Burji zones received light to moderate rainfall; Gida Ayana recorded heavy rainfall measuring 59.2 mm. On the other hand, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, and Kebridahar recorded high daytime temperatures ranging from 36.5 to 39.6°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ፋፈን፣ ቆራሄ፣ ዶሎ፣ ሸበሌ ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቄለምና ምስራቅ ወለጋ፣ ጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ማጃንግ፣ ከፋ፣ ሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በሰመራ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ፓዌ፣ መተማ፣ መተሐራ፣ መልካ ጀብዱ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, areas that benefit from the Belg season rains, as well as the western and northwestern parts of our country, will experience cloud cover. In association with this, many places within the following areas will receive light to moderate (1–29 mm) rainfall: From the Oromia region: West and East Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Iluababora, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, South West and West Shewa, and East and West Harerge zones; Harar and zones of Southern Ethiopia Region including Walayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso; all zones of the Sidama Region; from the Somali Region: Liben, Nogob, Afder, Fafan, Korahe, Dolo, Shebelle, Jarar and Erer zones; from the Central Ethiopia region: Gurage, Silte, a special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro zones; from Southwest Ethiopia: Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela: Agnuak, Nuer, Majang and Itang zones; from Benishangul Gumuz: Asosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones; and from Amhara: West and East Gojjam, Awi Zone, North, West, Central and South Gondar zones is expected in many places. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm in 24 hours is forecast for Kellem and East Wollega, Jimma, Buno Bedelle, Majang, Keffa, Sheka and Bench Sheko zones. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be highly beneficial for carrying out intensive agricultural activities. In contrast, in Semera, Gambella, Funyido, Abobo, Pawe, Metema, Metehara, Melka Jebdu, Dallifage, Awash Arba, Dire Dawa, Aisha, Kebridahar and Gode, daytime maximum temperatures are recorded as high, ranging from 35 to 40 degrees Celsius.