Daily Weather Report 26 May 17
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በምዕራብ ጉጂ፣ምስራቅ ቦረና፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ጌዴኦ፣ጉራጌ፣ አኝዋክ፣ ሸካ፣ ጎፋ፣ ሀዋሳ፣ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በማሻ 30.6 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተሐራ፣ ድሬዳዋ እና በመንደር11 የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-37.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, areas that benefit from the Belg season rains, as well as the western parts of our country, experienced cloud cover. In line with this, West Guji, East Borana, Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, East Wollega, East Gojjam, Awi zone, Gedeo, Gurage, Agnuwak, Sheka, Gofa, Hawassa, South Omo, and Konso zones received light to moderate rainfall, while a heavy rainfall amount of 30.6 mm was recorded in Masha. On the other hand, the daily maximum temperature in Metehara, Dire Dawa, and Village 11 was recorded between 35.0°C and 37.2°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር እና ቡኖ በደሌ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በሰመራ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ፓዌ፣ መተማ፣ መተሐራ፣ መልካ ጀብዱ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, areas that benefit from the Belg season rains, as well as the western and northwestern parts of our country, will experience cloud cover. In association with this, many places within the following areas will receive light to moderate (1–29 mm) rainfall: From the Oromia region: Guji, West Guji, Borana, East Borana, Bale, East Bale, Arsi, West Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem Wollega, East Wollega, West Wollega, Southwest Shoa, West Shoa, West Hararghe, and East Hararghe zones; Harari; from the South Ethiopia region: Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo, and Konso zones; all zones of the Sidama region; from the Somali region: Fafan and Jarar zones; from the Central Ethiopia region: Gurage, Silte, Yem special zone, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro zones; from the Southwest Ethiopia region: Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and West Omo zones; from the Gambella region: Agnuwak, Nuwer, Majang, and Itang zones; from Benishangul-Gumuz: Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao-Komo zones; and from the Amara region: West Gojjam, East Gojjam, Awi zone, North Gondar, West Gondar, Central Gondar, and South Gondar zones. Additionally, Keffa, Sheka, Bench Sheko, Jimma, Illubabor, and Buno Bedele zones will experience heavy rainfall of over 30 mm within 24 hours. Therefore, the expected rainfall amount and distribution will be highly beneficial for conducting Belg agricultural activities. On the other hand, the daily maximum temperature in Semera, Gambella, Fugnido, Abobo, Pawe, Metema, Metehara, Melka Jebdu, Dallifage, Awash Arba, Dire Dawa, Aysha, Kebridahar, and Gode will be recorded between 35 and 40 degrees Celsius.