Daily Weather Report 26 May 14

Weather Summary for previous day

May 13, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ማዕከላለዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ጋሞ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ ወላይታ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዴኦ፣ አዊ ዞን እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በቡሌ ሆራ፣ በደሌ፣ ቴፒ እና በቅዳሜ ገበያ 32.7-81.6ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተሐራ፣ ሰመራ፣ ፉኝዶ፣ መልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ኤሊዳር ፣ቀብሪደሃር እና አዲስ ዘመን የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-43.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

On the previous day, areas that benefited from widespread light rain, as well as parts of the western and northwestern regions of our country, experienced cloudy skies. In addition, Borena, Guji and West Guji, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, Central Gondar, West and East Gojjam, Gamo, Sheka, West Omo Wolayta, Burji, South Omo, Gedeo, Awi Zone and Agnuak Zones recorded light to moderate rainfall; heavy amounts of rain ranging from 32.7 to 81.6 mm were reported in Bule Hora, Bedelle, Tepi and Kedame Gebeya. Conversely, very high daytime maximum temperatures between 35.0 and 43.8°C were observed in Metehara, Semera, Funyido, Melka Jebdu, Dire Dawa, Dallifage, Awash Arba, Elidar, Kebridahar and Addis Zemen.

Weather Forecast for next day

May 15, 2026

በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ፋፈን እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌና ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በሰመራ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ፓዌ፣ መተማ፣ መተሐራ፣ መልካ ጀብዱ፣ መንደር11፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, weather system is expected to move across the country, bringing cloud cover to the Belg-beneficiary areas as well as the western and northwestern. Hence, light to moderate rainfall, measuring between 1mm and 29mm, is forecasted in parts of Oromia: Guji and western Guji, Borena and east Borena, Bale and east Bale, Arsi and west Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem, east and west Wollega, southwest Wollega, east Wollega and north Shewa, west and east Harerge zones; Harar; from Southern Nations, Nationalities, and Peoples' Region: Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alaba, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; across all zones of Sidama region; from Somali region: Dawa, Nogob, Afder, Fafan and Jarar zones; from Central Ethiopia region: Gurage and east Gurage, Mareko special zone, Silte, Marko special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro zones; from Southwest Ethiopia region: Kafa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela region: Agnuak, Nuer, Majang and Itang zones; from Benishangul-Gumuz: Asosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones; from Amhara region: West and East Gojjam, Awi zone, North, West, Central and South Gondar zones; and from Tigray region: Central, West and North West zones many of these areas will receive light to moderate rain amounts ranging from 1 to 29 mm. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected over Buno Bedelle, Jimma, western and eastern Shewa, and east and west Wollega zones. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great benefit for carrying out rainfed agricultural activities. On the other hand, in Semera, Gambella, Funyido, Abobo, Pawe, Metema, Metehara, Melka Jebdu, Mender 11, Dallifage, Awash Arba, Dire Dawa, Aisha, Kebri Dehar and Gode, daytime maximum temperatures are recorded between 35 and 40 degrees Celsius.