Daily Weather Report 26 May 13

Weather Summary for previous day

May 12, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በምስራቅ ቦረና፣ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ አሶሳ፣ ጅማ፣ ጋሞ፣ ወላይታ፣ ሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን ጎንደር፣ አኝዋክ እና ኮንሶ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በሀሮ 40.4ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተሐራ፣ መንደር11፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መተማ፣ ድሬዳዋ፣ ማይሀንሳ እና አዲስ ዘመን የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.0-39.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

The Belg rain-benefiting areas, as well as the western and northwestern parts of the country, experienced cloud cover during the previous day. In line with this light to moderate rainfall was recorded in eastern Borena, Guji and western Guji, western Wollega, Asosa, Jimma, Gamo, Wolayita, northwestern Tigray, Awi zone, North Gondar, Agnuak and Konso zones, with a heavy downpour of 40.4 mm recorded in Haro. Elsewhere, daytime maximum temperatures were recorded in Metehara, Mender 11, Gambella, Funyido, Metema, Dire Dawa, Mayhansa and Addis Zemen, ranging from 36.0 to 39.5°C.

Weather Forecast for next day

May 14, 2026

በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ሊበን፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ፋፈን፣ ቆራሄ፣ ዶሎ፣ ሸበሌ ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌና ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ቡኖ በደሌ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በሰመራ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ፓዌ፣ መተማ፣ መተሐራ፣ መልካ ጀብዱ፣ መንደር11፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, weather system is expected to move across the country, bringing cloud cover to the Belg-beneficiary areas as well as the western and northwestern. Hence, light to moderate rainfall, measuring between 1mm and 29mm, is forecasted for parts of Oromia including Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, Southwest Wollega, West and North Shewa, and West and East Harerge zones; Harari; from the Southern Nations, Nationalities, and Peoples’ Region: Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alle, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; all zones of the Sidama region; from Somali region: Dawa, Liben, Nogob, Afder, Fafan, Korahe, Dolo, Shebelle, Jarar and Erer zones; from the Central Ethiopia region: Gurage and East Gurage, Mareqo special zone, Silte special zone, Marko special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro zones; from the Southwestern Ethiopia region: Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela region: Agnuak, Nuer, Majang and Itang zones; from Benishangul-Gumuz: Asosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones; from Amhara: West and East Gojjam, Awi zone, North, West, Central and South Gondar zones; and from Tigray: Central, Western and North Western zones will receive light to moderate rain in many places, with amounts ranging from 1 to 29 mm. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected in Asosa, West Shewa, Buno Bedelle and West Wollega zones. Accordingly, the amount and distribution of rainfall will be highly beneficial for carrying out intensive agricultural activities. Meanwhile, in Semera, Gambella, Funyido, Abobo, Pawe, Metema, Metehara, Melka Jebdu, Mender 11, Dallifage, Awash Arba, Dire Dawa, Aisha, Kebridahar and Gode, daytime maximum temperatures are recorded between 35 and 40 degrees Celsius.