Daily Weather Report 26 May 12

Weather Summary for previous day

May 11, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ አሶሳ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ሸካ፣ ጋሞ፣ ወላይታ፣ ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በበደሌ እና በዴጋ ከ31.4-35.2ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ መተሐራ፣ መልካ ጀብዱ፣ መንደር11፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-40.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there was widespread light rain in many areas, with cloud cover over the western and northwestern parts of the country. In addition, the Borena, Assosa, Jimma, Iluababora, Buno Bedele, Western and Eastern Wollega, West Omo, Sheka, Gamo, Wolayita, Gedeo and South Omo zones received light to moderate rainfall, while heavy rains of 31.4–35.2 mm were recorded in Bedele and Dega. Elsewhere, the highest daytime temperatures were recorded in Samara, Metehara, Melka Jebdu, Mender 11, Dallifage, Awash Arba, Dire Dawa, Kebridahar and Gode, ranging from 35.0 to 40.4°C.

Weather Forecast for next day

May 13, 2026

በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ ሐረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ሊበን፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ፋፈን፣ ቆራሄ፣ ዶሎ፣ ሸበሌ ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌና ምስራቅ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ አሶሳ፣ ማኦኮሞ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ፓዌ፣ መልካ ጀብዱ፣ መተማ፣ አቦቦ፣ ማይሀንሳ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አዋሽ አርባ፣ አይሻ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, weather system is expected to move across the country, bringing cloud cover to the Belg-beneficiary areas as well as the western and northwestern: Hence, light to moderate rainfall, measuring between 1mm and 29mm, is forecasted from Oromia region Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem; East and West Wollega, South West Wollega, West, East and North Shewa, West and East Harerge zones; Harari; South West and West Shewa zones of Harar; from Southern Ethiopia Region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alle, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; all zones of the Sidama region; from Somali region Dawa, Liben, Nogob, Afder, Fafan, Korahe, Dolo, Shebelle, Jarar and Erer zones; from Oromia zonal areas of the Central Ethiopia region Gurage and East Gurage, Silte, the special Mareko zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro zones; from South West Ethiopia Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela region Agnuak, Nuer, Majang and Itang zones; from Benishangul-Gumuz Assosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; from Amhara region West and East Gojjam, Awi zone, North, West, Central and South Gondar zones; and from Tigray region West and North West zones. In addition, the Jimma, Assosa, Mao Komo, West Shewa, Illubabor, Buno Bedelle, Kellem, and East and West Wollega zones are expected to experience heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be highly beneficial for conducting rainfed agricultural activities. On the other hand, in Semera, Pawe, Melka Jebdu, Metema, Abobo, Mayhanssa, Gambela, Funyido, Awash Arba, Aisha, Kebridahar and Gode, daytime maximum temperatures are recorded to be high, ranging from 35 to 40 degrees Celsius.