Daily Weather Report 26 May 09
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሸካ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ደቡብ ኦሞ እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ መተሐራ፣ ድሬዳዋ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.5-38.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
During the previous day, cloud cover was observed over the areas that typically benefit from the Belg rains as well as western parts of the country. In association with this, several zones including West Guji, Borena, Jimma, Illubabor, East Wollega, and West Hararghe, as well as Sheka, Wolayita, Gamo, South Omo, and Agnuwak received light to moderate rainfall. On the other hand, maximum daily temperatures were recorded in Fugnido, Metehara, Dire Dawa, and Gode, ranging between 35.5°C and 38.8°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ቆራሄ፣ ዶሎ እና ሸበሌ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌና ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በኢሉባቦር፣ ቄለምና ምስራቅ ወለጋ፣ ሸካ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ መተሐራ፣ ፓዌ፣ ድሬዳዋ፤ ማይሀንሳ፣ አዲስ ዘመን፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ጨዋቃ፣ መልካ ጀብዱ፣ አዋሽ አርባ፣ ላይ በር፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, cloud cover is expected over the Belg rainfall benefiting areas as well as the western and northwestern parts of the country. In association with this, light to moderate rainfall amounting to 1–29 mm is expected over many areas of Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, West Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, Southwest Shewa, and West Shewa zones of the Oromia Region; Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo, and Konso zones of the South Ethiopia Region; all zones of the Sidama Region; Dawa, Liben, Nogob, Afder, Korahe, Dolo, and Shebelle zones of the Somali Region; Gurage and East Gurage, Mareko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, and Kembata Tembaro zones of the Central Ethiopia Region; Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and West Omo zones of the Southwest Ethiopia Region; Agnuwak, Nuer, Majang, and Itang zones of the Gambella Region; Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao Komo zones of the Benishangul Gumuz Region; West and East Gojjam, Awi Zone, West, North, Central, and South Gondar zones of the Amhara Region; and the Western and Northwestern zones of the Tigray Region. A more significant weather event is expected in Illubabor, Kelem, East Wollega, Sheka, Assosa, and Mao-Komo, where heavy rainfall exceeding 30 mm is predicted within a 24-hour period. Therefore, the anticipated rainfall amount and distribution will have significant importance for carrying out Belg season agricultural activities. On the other hand, maximum daily temperatures ranging from 35°C to 40°C are expected to be recorded in Semera, Metehara, Pawe, Dire Dawa, Mayhansa, Addis Zemen, Gambella, Fugnido, Chewaka, Melka Jebdu, Awash Arba, Layber, Kebri Dehar, and Gode.