Daily Weather Report 26 May 08

Weather Summary for previous day

May 7, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም ፣ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ ፤ ምዕራብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ አኙዋክ፣ መተከል፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ማዕከላዊና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ ማጃንግ፣ ሸበሌ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአማን፣ ጨዋቃ፣ ዳንግላ፣ ደሎ መና፣ በሊሙ ገነት እና በቀርሳ ከ30.1-53.2ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ መተሐራ፣ ፓዌ፣ ድሬዳዋ፤ ማይሀንሳ፣ አዲስ ዘመን፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ጨዋቃ፣ መልካ ጀብዱ፣ አዋሽ አርባ፣ ላይ በር፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-41.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there was beneficial light rain in many areas, and cloudy skies over the western and northwest parts of the country. In addition, places including Borena, Bale, West Guji, Jimma, Iluababora, Buno Bedele, Kellem, West and East Wollega, West Harerge, West Omo, Wolayita, Agnuak, Metekel, North, Central and South Gondar, East Gojjam, Awi zone, Central and North West Tigray, Majang, Shebele, and South Omo zones received light to moderate rainfall. Heavy rainfall measuring between 30.1 and 53.2 mm was recorded at Amaro, Chewaka, Dangila, Delo Mena, Lemmu Genet and Kersa. Meanwhile, high daytime temperatures between 35.0 and 41.2°C were recorded at Semera, Metehara, Pawe, Dire Dawa, Mayhanssa, Addis Zemen, Gambella, Funyido, Chewaka, Melka Jebdu, Awash Arba, Lay Ber, Kebridahar and Gode.

Weather Forecast for next day

May 9, 2026

በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል በጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ዶሎ፣ ኤረር፣ እና ቆራሄ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌና ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሸካ፣ከፋ፣ ቄለም ወለጋ፣ጂማ፣ ኮንታ፣ኢሉባቦር፣አዊ ዞን እና ቡኖ በደሌ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ጠቀሜታ ይኖረዋል። በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ አሸሬ፣ አዲስ ዘመን፣ ጨዋቃ፣ መተሐራ፣ ቀብሪደሃር፣ መተማ፣ ሸርኮሌ፣ ገዋኔ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40°C ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, cloud cover is expected over the areas benefiting from the Belg rains, as well as the western and northwestern parts of the country. In connection with this, many places in the Oromia Region,Guji and West Guji, Borena and East Borena, Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, Arsi and West Arsi, Southwest and West Shewa, and West and East Hararghe zones; Harar; Dire Dawa; the South Ethiopia Region zones of Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alle, Kore, Gardula, South Omo, and Konso; all zones of the Sidama Region; the Somali Region zones of Dawa, Siti, Fafan, Jarar, Dolo, Erer, and Korahe; the Central Ethiopia Region zones of Gurage and East Gurage, Mareko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro; the Southwest Ethiopia Region zones of Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and West Omo; the Gambella Region zones of Majang, Nuwer, Agnuak, and Itang; the Benishangul-Gumuz Region zones of Metekel, Assosa, Kamashi, and Mao-Komo; the Amhara Region zones of West and East Gojjam, Awi, West, North, Central, and South Gondar; and the Tigray Region West and Northwest zones will receive light to moderate rainfall (1–29 mm) on their many places. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm is expected within 24 hours in the Sheka, Keffa, Kelem Wollega, Jimma, Konta, Illubabor, Awi, and Buno Bedele zones. Consequently, the amount and distribution of the rainfall will be beneficial for performing Belg agricultural activities. On the other hand, in Gambella, Mayhanssa, Yechila, Ashere, Addis Zemen, Chawaka, Metehara, Kebridahar, Metema, Sherkole, Gewane, Semera, Elidar, and Gode, the daily high temperature will be recorded between 35-40°C.