Daily Weather Report 26 May 07

Weather Summary for previous day

May 6, 2026

በትናንትናው ዕለት በምስራቅ፣ በደቡብ፣ በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከፍተኛ የደመና ሽፋን የነበረ ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በምዕራብ ጉጂ፣ በባሌና ምስራቅ ባሌ፣ በምስራቅ ሐረርጌ፣ በምዕራብ ጎጃም፣ በሰሜንና ደቡብ ጎንደር እንዲሁም በጌዴኦ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል። በተለይም በዲላ አካባቢ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ የዘነበ ሲሆን፤ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በመልካ ጀብዱ፣ በአይሻ፣ በመተሐራ እና በማይሀንሳ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-41.0 °C ሆኖ ተመዝግቧል።

Yesterday, there was cloud cover over the eastern, southern, western, and northwestern parts of the country. In connection with this, light to moderate rainfall was recorded in West Guji, Bale and East Bale, East Hararghe, West Gojjam, North and South Gondar, as well as the Gedeo zones. Additionally, a high amount of rainfall was recorded in the Dilla. On the other hand, high daily temperatures ranging from 35.0–41.0°C were recorded in Gambella, Melka Jebdu, Aisha, Metehara, and Mayhansa.

Weather Forecast for next day

May 8, 2026

በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን ክፍሎች ላይ ከፍተኛ የደመና ሽፋን የሚኖር ሲሆን፣ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ኖጎብ፣ ሊበን፣ ዳዋ፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ደቡብ ኦሞ እና በኮንሶ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና የዳዉሮ ዞኖች፣ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ የምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን እና ከምባታ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር እና ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ። በተመሳሳይ ሁኔታ በምስራቅ ወለጋ፣ በሸካ፣ በቤንች ሸኮ፣ በመተከል፣ በቡኖ በደሌ፣ በአዊ እና በፋፈን ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ የሚኖር ሲሆን፣ በሌላ በኩል በማይሀንሳ፣ በየጭላ፣ በአሸሬ፣ በአዲስ ዘመን፣ በጨዋቃ፣ በመተሐራ፣ በቀብሪደሃር፣ በመተማ፣ በሸርኮሌ፣ በገዋኔ፣ በሰመራ፣ በኤሊዳር እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ይመዘገባል።

Tomorrow, there will be cloud cover over the Belg-rain-beneficiary areas as well as the western and northwestern parts of the country. In connection with this, from the Somali region: Siti, Fafan, Nogob, Liben, Dawa, Jarar, Erer, Afder, Shebelle, Korahe, and Dolo zones; from the Southern Ethiopia region: Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alle, Kore, Gardula, South Omo, and Konso zones; from the Southwest Ethiopia region: Bench Sheko, Sheka, Keffa, Konta, West Omo, and Dawuro zones; from the Oromia region: Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, East and West Hararghe, Arsi and West Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wollega, and West and Southwest Shewa zones; the zones of the Sidama region; from the Central Ethiopia region: Gurage, Hadiya, Yem special zone, and Kembata zones; from the Benishangul-Gumuz region: Metekel, Assosa, Kamashi, and Mao-Komo zones; from the Gambella region: Majang, Nuer, Agnuak, and Itang zones; from the Amhara region: North, West, Central, and South Gondar, and West and East Gojjam; and from the Tigray region: the West and Northwest zones, will receive light to moderate rainfall (1–29 mm) in many of areas. Additionally, heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours is expected in East Wollega, Sheka, Bench Sheko, Metekel, Buno Bedele, Awi, and Fafan zones. On the other hand, high daily temperatures ranging from 35–40°C will be recorded in Mayhansa, Yechila, Ashere, Addis Zemen, Chewaka, Metehara, Kebridahar, Metema, Sherkole, Gewane, Semera, Elidar, and Gode.