Daily Weather Report 26 May 04

Weather Summary for previous day

May 3, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች እንዲሁም በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል የደመና ሽፋን ነበራቸው። ከዚሁም ጋር ተያይዞ ምዕራብ ጉጂ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ደቡብ ኦሞ እና ቡርጂ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፣ አርሲ ሮቤ፣ በአዲስ አበባ፣ ቡኢ፣ ሀርሽን እና በአቃቂ ከ33.2-85.2 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ መተሐራ ፣አዲስ ዘመን እና በማይሀንሳ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.8-41.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud cover was observed over the Belg-rain beneficiary areas as well as the northern parts of the country. In line with this, West Guji, Southwest, West, East and North Shewa, West Hararghe, East Gojjam, North Gondar, North and South Wollo, Wolayita, Gamo, South Omo, and Burji received light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall ranging from 33.2-85.2 mm was recorded in Arsi Robe, Addis Ababa, Bui, Harshin, and Akaki. Meanwhile, maximum daily temperatures between 35.8-41.8°C were registered in Gambella, Fugnido, Semera, Metehara, Addis Zemen, and Mayhansa.

Weather Forecast for next day

May 5, 2026

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛና የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በተለይም በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት የሚኖራቸው ሲሆን፤ በምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይም የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ኖጎብ፣ ሊበን፣ ዳዋ፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን እና ከምባታ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ቄለም ወለጋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ፣ባሌ እና ኤረር ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በ ማይሀንሳ፣ የጭላ፣ አሸሬ፣ አዲስ ዘመን፣ ጨዋቃ፣ መተሐራ፣ ቀብሪደሃር፣ መተማ፣ ሸርኮሌ፣ ገዋኔ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40°C ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, strong cloud cover and accumulation will prevail over the primary Belg rain-beneficiary regions, particularly in the southern, southwestern, and southeastern parts of the country; additionally, cloud cover will be present over the northwestern regions. In connection with this, Somali region Sitti, Fafan, Nogob, Liben, Dawa, Jarar, Erer, Afder, Shaballe, Korahe, and Dolo zones; the South Ethiopia region Wolayta, Gofa, Gamo, Basketo, Burji, Konso, Kore, Gardula, South Omo, and Gedeo zones; the Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Keffa, Konta, West Omo, and Dawuro zones; and the Oromia region Guji, West Guji, Borena, East Borena, Bale, East Bale, East and West Hararghe, Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, Kelem, Horro Guduru, and West and East Wollega zones, the Sidama region zones; the Central Ethiopia region Hadiya, Yem special zone, and Kembata zones; the Gambella region Majang, Nuer, Agnuak, and Itang zones; and the Amhara region North, Central, and South Gondar, and West Gojjam zones will receive similar rainfall light to moderate rainfall ranging from 1–29 mm. Furthermore, the Kelem Wollega, Sheka, Bench Sheko, Shaballe, Korahe, Bale, and Erer zones are expected to receive heavy rainfall exceeding 30 mm within a 24-hour period. Conversely, high daytime temperatures ranging between 35–40°C will be recorded in Mayhansa, Yechila, Ashere, Addis Zemen, Chewaka, Metehara, Kebridahar, Metema, Sherkole, Gewane, Semera, Elidar, and Gode.