Daily Weather Report 26 May 03
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ጅማ፣ አዲስ አበባ፣ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ደቡብ ኦሞ እና ቡርጂ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በኩሉምሳ እና በሳውላ ከ39.0-65.2ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.8-37.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
On the previous day, areas of the country that benefited from Belg rain were cloudy. In line with this, in Borena, West Guji, South West, West, East and North Shewa, West and East Hararghe, Bale, Jimma, Addis Ababa, Harar, Dire Dawa, East Gojjam, North Gondar, North and South Wallo, Gurage, Wolayita, South Omo and Burji received light to moderate rain. Heavy rainfall of 39.0–65.2 mm was recorded in Kulumsa and Sawla. Meanwhile, Gambela and Gode recorded the daytime maximum temperatures, ranging from 35.8 to 37.4°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ቆራሄ፣ ፋፈን፣ ጃራር ፣ ዶሎ፣ ሸበሌ እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ጅማ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ፣ ጃራር እና ዶሎ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ሸርኮሌ፣ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ እና በአዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Cloud cover is expected over areas that benefit from the Belg rains, as well as over the western and northwestern parts of the country for tomorrow. In line with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in many places of Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, Southwest, West and North Shewa; East and West Hararghe zones of Oromia region; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alle, Kore, Gardula, Burji, South Omo, and Konso zones of South Ethiopia region; across all zones of Sidama region; Dawa, Liben, Afder, Korahe, Fafan, Jarar, Dolo, Shaballe, and Erer zones of Somali region; Gurage, Silte, Yem Special zone, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro zones of Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and West Omo zones of Southwest Ethiopia Region; Anyuwaak, Majang, and Itang zones of Gambella region; Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao Komo zones of Benishangul Gumuz; West, North, and East Gojjam, Awi zone, West, North, Central, and South Gondar, North and South Wollo, and Wag Hemra zones of Amhara region; East, Southeast, South, Central, West, and Northwest zones of Tigray region. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected in Bench Sheko, Kaffa, Jimma, Konta, Dawuro, Jarar, and Dolo zones. Therefore, the expected amount and distribution of rainfall will have significant benefits for Belg-season agricultural activities. On the other hand, the daily maximum temperature is expected to range between 35 and 40 degrees Celsius in Metema, Sherkole, Gambella, Fugnido, Abobo, Gode, Kebri Dehar, Semera, Elidar, Gewane, and Awash Arba.