Daily Weather Report 26 May 02

Weather Summary for previous day

May 1, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፤ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በድሬዳዋ፤ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መተሐራ፣ መንደር 11 እና መልካ ጀብዱ፣ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-38.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday many parts of the country that benefitted from Belg light rain were cloudy. In addition, areas including Borena East, Borena West Guji, West and East Shewa, Addis Ababa, Dire Dawa, Bono Bedele, East Gojjam, North and South Wollo, Gurage, Wolayita, Gamo, Basketo, Gedeo, South Omo and Konso reported light to moderate rainfall. Elsewhere, in Dire Dawa, Gambela, Funyido, Metehara, Mender 11 and Melka Jebdu the daytime maximum temperature was recorded between 35 and 38.5°C.

Weather Forecast for next day

May 3, 2026

በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ቆራሄ፣ ፋፈን፣ ሲቲ፣ ጃራር፣ ዶሎ፣ ሸበሌ እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በኢሉባቦር፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ጅማ፣ ማዕከላዊ ትግራይ ዞን እና የም ልዩ ዞን በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ሸርኮሌ፣ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ እና በአዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ።

Tomorrow cloudy conditions are likely over Belg season benefiting areas also parts of the western and northwestern of the country. In line with this from Oromia Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem; East and West Wollega, Southwest Wollega, West and North Shewa, West and East Hararghe zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from Southern Ethiopia Region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alle, Kora, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; all zones of Sidama region; from Somali Region Dawa, Liben, Afder, Korahe, Fafan, Sitti, Jarar, Dolo, Shebelle and Erer zones; from Central Ethiopia Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yeem special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro zones; from Southern Southwest Ethiopia Kafa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela Agnuak, Majang and Itang zones; from Benishangul-Gumuz Asosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komodo zones; from Amhara West, North and East Gojjam, Awi zone, West, North, Central and South Gondar, North and South Wollo and Wag Hemra zones; and from Tigray East, South, Central, West and North West zones. In many of these places rainfall amounts are expected to range from light to moderate, about 1–29 mm. Additionally, heavy rain exceeding 30 mm within 24 hours is likely in Illubabor, Sheka, Bench Sheko, Kafa, Jimma, Central Tigray zone and the Yeem special zone. Accordingly, the amount and distribution of rainfall will be of great benefit for carrying out Belg season farming activities. On the other hand, in Metema, Sherkole, Gambella, Fugnido, Abobo, Gode, Kebridahar, Semera, Elidar, Gewane and Awash Arba, our weather forecast information indicates that daytime maximum temperatures will be registering between 35 and 40 degrees Celsius.