Daily Weather Report 26 March 30
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ጠንካራ የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ ሐዋሳ፣ ኢሉባቦር፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በጨለንቆ፣ ጊዶሌ፣ ሐራ እና ደብረ ሲና ከ30-71.0 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣መተማ፣ አሸሬ፣ አሺ፣ መንደር 11፣ እና የጭላ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there were strong cloud cover in the areas that benefited from the belg rains and in the western part of the country. In addition, Borena, Bale and East Bale, Arsi, Guji and West Guji, West and East Hararge, West, East, South West and North Shewa, Hawassa, Ilubabor, East Wellega, East Gojam, North and South Wello and North Shewa received light to moderate rainfall; Chelenko, Gidole, Hara and Debre Sina received heavy rainfall of 30-71.0 mm. On the other hand, Gambella, Metema, Ashere, Ashi, Village 11, and Yecla received daily maximum temperatures of 35-40.0°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ቆራሄ፣ ፋፈን፣ ሲቲ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ እና የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የፋንቲ እና ሀሪ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም በሸካ፣ ከፋ፣ ዳውሮ፣ ጉራጌ ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጉጂ እና አርሲ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ሸርኮሌ፣ ኩምሩክ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, there will be strong cloud cover and accumulation in the areas that benefit from the belg rains and in the western and northwestern parts of our country. In connection with this, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wellega, Southwest, West, East and North Shewa, West and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa; From the Southern Ethiopian Region: Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; from all zones of Sidama Region; from the Somali Region: Dawa, Liben, Afder, Korahe, Fafen, Siti, Jarar and Erer zones; from the Central Ethiopian Region: Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones; from the Southwestern Ethiopian Region: Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dauro and West Omo zones; from the Gambella Region: Anwak and Majang zones; West, North and East Gojam, Central and South Gondar, North and South Wollo, Waghemra and the Oromo Nationality Special Zone of the Amhara Region; The Central and Northwestern zones of Tigray region; Fanti and Hari zones of Afar region will receive light to moderate (1-29mm) rainfall in many places. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out belg agricultural activities. In addition, Sheka, Kefa, Dawro, Gurage, East and West Hararge, Guji and Arsi will have heavy rainfall of more than 30mm in 24 hours in some places. On the other hand, in Metema, Sherkole, Kumruk, Gambella, Fugendo, Abobo, Gode, Kebridehar, Gewane and Awash Arba, the maximum daily temperature will be recorded as 35 to 40 degrees Celsius.