Daily Weather Report 26 March 29

Weather Summary for previous day

March 28, 2026

በትናንትናዉ ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ ሐዋሳ፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ጋምቤላ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በደምቢ ዶሎ፣ ቡሬ፣ ነቀምቴ እና ባቲ ጣቢያዎች ላይ ከ30-60.0ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ፉኝዶ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-39.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there were strong cloud cover over the areas of the country that benefited from the Belg season rains. Along with this, Borena, East Bale, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, East Hararge, West, East, South West and North Shewa, Hawassa, Addis Ababa, Dire Dawa, Harar, Buno Bedele, Ilubabor, Horo Guduru, East and West Wellega, Gambella, East Gojam, South Gondar, North and South Wello and North Shewa received light to moderate rainfall; Dembi Dolo, Bure, Nekemte and Bati stations received heavy rainfall of 30-60.0 mm. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded at 35-39.2°C in Gambella, Fugnido and Gode.

Weather Forecast for next day

March 30, 2026

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ፣ አማሮ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ቆራሄ፣ ፋፈን፣ ሲቲ፣ ጃራር፣ ዶሎ እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ዞን፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ እና ጋቢ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብ ሸዋ፣ ጃራር፣ ሸበሌ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብ ጉጂ እና ሲዳማ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ሸርኮሌ፣ ኩምሩክ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, there will be strong cloud cover and accumulation in the main and second rainy seasons of our country. In addition, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, East and West Wollega, Southwest, West, East and North Shewa, West and East Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; in the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gamo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo, Amaro and Konso zones; in all Sidama region zones; in the Somali region, Dawa, Liben, Afder, Korahe, Fafen, Siti, Jarar, Dolo and Erer zones; From the Central Ethiopian Region, Gurage, East Gurage, Mareko Special Zone, Silte, Mem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones; the Kefa, Sheka and Bench Sheko zones of the Southwestern Ethiopian Region; the Agniwak zone of the Gambella Region; the West, North and East Gojam, Central, North and South Gondar, North and South Wallo, Waghimra, Oromo National Special Zone and North Shewa zones of the Amhara Region; the Central, South East and North West zones of the Tigray Region; the Kelbeti, Fanti and Gabi zones of the Afar Region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. In addition, there will be heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours at a few places in West Shewa, Jarar, Shebele, West Hararge, Arsi and West Arsi, Bale, West Guji and Sidama. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out autumn agricultural activities. On the other hand, the highest daily temperatures in Metema, Sherkole, Kumruk, Gambella, Fugnido, Abobo, Gode, Kebridehar, Gewane and Awash arba will be recorded as 35 to 40 degrees Celsius.