Daily Weather Report 26 March 27

Weather Summary for previous day

March 26, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ጠንካራ የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ ሐዋሳ፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ ጋምቤላ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በ15 ጣቢያዎች ላይ ከ30-84.2 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ፉኝዶ፣ ሸርኮሌ፣ ማይሃንሳ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there were strong cloud cover in the areas that benefited from the belg rains and in the western part of the country. In connection with this, Borena, Bale and East Bale, Arsi, Guji and West Guji, West and East Hararge, West, East, South West and North Shewa, Hawassa, Addis Ababa, Dire Dawa, Harar, Buno Bedele, Ilubabor, Kelem Wellega, Gambella, East Gojam, North and South Wello and North Shewa received light to moderate rainfall; 15 stations received heavy rainfall ranging from 30-84.2 mm. On the other hand, Gambella, Fugendo, Sherkole, Mayhansa, Semera, Elidar and Gode recorded the highest temperature of the day at 35-40.5°C.

Weather Forecast for next day

March 28, 2026

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ቆራሄ፣ ፋፈን፣ ሲቲ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ አውሲ እና ጋቢ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም በአዲስ አበባ፣ ሲቲ ዞን፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ጉራጌ፣ ሀሪ፣ ፋንቲ፣ ምስራቅና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ቡኖ በደሌ ዙርያ እና አርሲ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ ይህም ሁኔታ ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ማህበረሰቡ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲወስዱ ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be strong cloud cover and accumulation in the main and second rainy seasons of the belg, as well as in the western and northwestern parts of our country. In addition, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, Southwest, West, East and North Shewa, West and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa, in the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; in all zones of Sidama region; The Dawa, Liben, Afder, Korahe, Fafen, Siti, Jarar and Erer zones from the Somali Region; the Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones from the Central Ethiopia Region; the Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawro and West Omo zones from the Southwestern Ethiopia Region; the Anwak, Majang, Nuer and Itang zones from the Gambella Region; the Asosa, Kamash and Maokomo zones from the Benishangul Gumuz Region; the West, North and East Gojam, Central and South Gondar, North and South Wollo, Waghemra, Oromo Nationality Special Zone and North Shewa zones from the Amhara Region; The Central, East, Southeast, South, Central, West and Northwest zones of Tigray region; the Kelbeti, Fanti, Awsi and Gabi zones of Afar region will receive light to moderate (1-29mm) rainfall in many places. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out belg agricultural activities. In addition, Addis Ababa, City Zone, Sheka, Kefa, Gurage, Hari, Fanti, East and Southwest Shewa, Buno Bedele Zuria and Arsi will have heavy rainfall of more than 30mm in a few places within 24 hours. This situation may cause flash floods, so the Ethiopian Meteorological Institute advises the community and relevant parties to take appropriate precautions.