Daily Weather Report 26 March 26

Weather Summary for previous day

March 25, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ሐዋሳ፣ አዲስ አበባ፣ ሐረር፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በቡኢ፣ ወራቤ፣ጂንካ፣ ነገሌ፣ ቡልቂ፣ አዳሚቱሉ፣ ሁንቴ እና ተልተሌ ከ30-43.6 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ፉኝዶ፣ አዲስ ዘመን፣ የጭላ፣ ማይሃንሳ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-39°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was heavy cloud cover in the western parts of the country, which benefited from the belg rains. In addition, Borena, Bale and East Bale, Arsi, Guji and West Guji, West and East Hararge, West, South West Shewa, Hawassa, Addis Ababa, Harar, Ilubabor, Kelem Wellega, Gambella, Asosa, North and South Wollo and North Shewa received light to moderate rainfall; Bui, Warabe, Jinka, Negele, Bulki, Adamitulu, Hunte and Teltele received heavy rainfall of 30-43.6 mm. On the other hand, Gambella, Fugendo, Addis Zemen, Yecla, Mayhansa, Kebridehar and Gode recorded the highest temperature of the day at 35-39°C.

Weather Forecast for next day

March 27, 2026

በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ እንደሚጠናከሩ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ቆራሄ፣ ፋፈን፣ ሲቲ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ አውሲ እና ጋቢ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በድሬዳዋ፣ ሲቲ ዞን፣ ሸካ፣ ከፋ፣ በደሌ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞን በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ሸርኮሌ፣ ኩምሩክ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, rain-bearing weather systems will intensify and continue over the main and second Belg rainfall areas, as well as over the western and northwestern parts of the country. In addition, from the Oromia region, the zones of Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, South West, West, East and North Shewa, West and East Hararge; Addis Ababa; Harar; from the Southern Ethiopia region, the zones of Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso; in all zones of Sidama region; from the Somali region, the zones of Dawa, Liben, Afder, Korahe, Fafen, Siti, Jarar and Erer; From the Central Ethiopian Region, Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro Zones; from the Southwestern Ethiopian Region, Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawro and West Omo Zones; The Anwak, Majang, Nuer and Itang zones of Gambella region; the Asosa, Metekel, Kamash and Maokomo zones of Benishengul Gumuz; the West, North and East Gojam, Awi, West, North, Central and South Gondar, North and South Wollo, Waghemra, Oromo National Special Zone and North Shewa zones of Amhara region; the Central, East, Southeast, South, Central, West and North West zones of Tigray region; the Kelebeti, Fanti, Awsi and Gabi zones of Afar region will receive light to moderate (1-29mm) rainfall in many places. In addition, Dire Dawa, City Zone, Sheka, Kefa, Bedele, Hari and Fanti Zones will experience heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out Belg agricultural activities. On the other hand, in Metema, Sherkole, Kumruk, Gambella, Fugendo, Abobo, Gode, Kebridehar, Gewane and Awash Arba, the maximum temperature of the day will be recorded as 35 to 40 degrees Celsius.