Daily Weather Report 26 March 25
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ሐዋሳ፣ አዲስ አበባ፣ ሐረር፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ ማጃንግ፣ ሸካ፣ አሶሳ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በማጀቴ፣ ወራቤ፣ ማሻ፣ አርባምንጭ፣ ጂንካ፣ ጊንር፣ ሰዲቃ እና ተልተሌ ከ30ሚሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ፉኝዶ፣ አዲስ ዘመን፣ መተማ፣ ፓዌ፣ የጭላ፣ ማይሃንሳ፣ ኤሊዳር፣ ሰመራ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover in the areas that benefited from the belg rains and in the western part of the country. In connection with this, Borena, Bale and East Bale, Arsi, Guji and West Guji, West and East Hararge, West, South West Shewa, Hawassa, Addis Ababa, Harar, Ilubabor, Kelem Wellega, Majang, Sheka, Asosa, North and South Wello and North Shewa received light to moderate rainfall, while Majete, Warabe, Masha, Arbaminch, Jinka, Ginr, Sediqa and Teltele received heavy rainfall of more than 30 mm. On the other hand, the highest daily temperatures in Gambella, Fugendo, Addis Zemen, Metema, Pawe, Yecla, Mayhansa, Elidar, Semera, Awash Arba, Gewane, Kebridehar and Gode were recorded at 35-40.5°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት፣ እንዲሁም በምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ሲቲ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ አውሲ፣ ሀሪ እና ጋቢ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፣ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ደግሞ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ ስርጭት የበልግ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን፣ እንዲሁም ለአርብቶ አደር አካባቢዎችም ለእንስሳት መኖና ለመጠጥ ውሀ አቅርቦትን ለማሻሻል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል። በሌላ በኩል በመተማ፣ ሸርኮሌ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል።
Tomorrow, there will be widespread cloud cover over the main and second rainy seasons of the belg, as well as over the western and northwestern areas of our country. In addition, in the Oromia region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wellega, Southwest, West, East and North Shewa, West and East Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from the Southern Ethiopian Region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; from all Sidama Region zones; from the Somali Region, Fafen, Siti, Jarar and Erer zones; from the Central Ethiopian Region, Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Silte, M Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones; from the Southwestern Ethiopian Region, Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dauro and West Omo zones; from the Gambella Region, Anwak, Majang, Nuer and Itang zones; from the Benishengul Gumuz, Asosa, Metekel, Kamash and Maokomo zones; From the Amhara region, the West, North and East Gojam, Awi, West, North, Central and South Gondar, North and South Wollo, Waghema, Oromo National Special Zone and North Shewa zones; The East, Southeast, South, Central, West and Northwest zones of Tigray region; the Kelbeti, Fanti, Awsi, Hari and Gabi zones of Afar region will receive light to moderate (1-29mm) rainfall in most places, and heavy rainfall in a few places. Therefore, the rainfall distribution will be of great importance for carrying out autumn agricultural activities, as well as improving the supply of fodder and drinking water for pastoral areas. On the other hand, the maximum temperature in Metema, Sherkole, Gambella, Fugendo, Abobo, Gode, Kebridehar, Semera, Elidar, Gewane and Awash Arba will be recorded as 35 to 40 degrees Celsius.