Daily Weather Report 26 March 24

Weather Summary for previous day

March 23, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተስፋፋ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ሐዋሳ፣ አዲስ አበባ፣ ሐረር፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ ማጃንግ፣ ሸካ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ አሶሳ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በሞላሌ እና ጅማ ከ30ሚሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ መንደር 11፣ ማይሃንሳ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

yesterday There was widespread cloud cover in the western parts of the country, which benefited from the belg rains. In addition, Borena, Bale and East Bale, Arsi, Guji and West Guji, West and East Hararge, West, South West Shewa, Hawassa, Addis Ababa, Harar, Ilubabor, Kelem Wellega, Majang, Sheka, East Gojam, Asosa, North and South Wello and North Shewa received light to moderate rainfall, while heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Molale and Jimma. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded at 35-40°C in Gambella, Village 11, Mayhansa, Semera, Gewane and Gode.

Weather Forecast for next day

March 25, 2026

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ፋፈን፣ ሲቲ እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ እና ሀሪ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በበደሌ ዙርያ፣ ቦረቻ፣ ደዴሳ፣ ሊሙ ሰቃ፣ ሁርሙ፣ ያዩ፣ ሰተማ፣ ጌሻ፣ ገራ እና ገውታ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ሸርኮሌ፣ ኩምሩክ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ።

Tomorrow, there will be cloud cover in the main and second rainy seasons of the belg and in the western parts of our country. In connection with this, in the Oromia region, Guji and West Guji, Bore, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wellega, South West, West, East and North Shewa, West and East Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; From the Southern Ethiopian Region: Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso Zones; from all Sidama Region Zones; from the Somali Region: Dawa, Fafen, Siti and Jarar Zones; from the Central Ethiopian Region: Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Silte, Mm Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro Zones; from the Southwestern Ethiopian Region: Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dauro and West Omo Zones; from the Gambella Region: Anwak, Majang, Nuer and Itang Zones; from the Benishengul Gumuz: Asosa, Metekel, Kamash and Maokomo Zones; The West and East Gojam, Awi, West, North and South Wollo, Oromo National Special Zone and North Shewa zones of Amhara region; the East, South East and South zones of Tigray region; and the Kelbeti and Hari zones of Afar region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. In addition, Bedele Zuria, Boracha, Dedesa, Limu Seka, Hurmu, Yau, Setema, Gesha, Gera and Gewta will experience heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, our numerical forecast data indicates that the maximum daily temperature in Metema, Sherkole, Kumruk, Gambella, Fugendo, Abobo, Gode, Kebridehar, Semera, Elidar, Gewane and Awasharba will be recorded as 35 to 40 degrees Celsius.