Daily Weather Report 26 March 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተስፋፋ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ቦረና፣ ባሌ፣ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አዲስ አበባ፣ ሐረር፣ድሬዳዋ፤ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም እና ምስራቅ ወለጋ፣ ኢታንግ ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ ሰሜን፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ፣ምስራቅ ጎጃም እና ምስራቅ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በሻምቡ፣ ሊሙ ገነት፣ ሀዋሳ፣ ወራቤ ፣ ባቱ ፣ አርሲ ሮቤ፣ አቦምሳ፣ መተሐራ እና ገለምሶ ከ30ሚሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ37.5-40.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there was beneficial widespread light rain, and there were extensive cloud patches over the northwest and western parts of the country. In addition, rain fall in Jimma, Borena, Bale, Guji and western Guji, western and eastern Harerge, north, west, southwest and east Shewa, Addis Ababa, Harar, Dire Dawa, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem and eastern Wollega, Itang, Sheka, western Omo, Walayita, Gurage, northern, central and southern Gondar, northern and southern Wollo, Waghemra, the special zone of the Oromia people, northern Shewa, eastern Gojjam and eastern Tigray, ranging from light to moderate intensity. Heavy rainfall exceeding 30 mm was recorded at Shambu, Limu Genet, Hawassa, Werabe, Batu, Arsi Robe, Abomsa, Metehara and Gelemso. Elsewhere, extremely high daytime temperatures of 37.5–40.0°C were recorded at Gambela, Funyido and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተስፋፋና ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር ፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ፋፈን፣ ሲቲ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ ሀሪ እና ጋቢ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ ራሬ፣ ሚዳ ቃኝ፣ ግንደበረት፣ ባኮ ቲቤ፣ ጫሊያ እና ኢሉ ጋላን በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ሸርኮሌ፣ ኩምሩክ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ካማሽ፣ ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ።
Tomorrow, there will be rain Bering weather and cloud cover over the belg main and second rainy seasons of our country also, western and northwestern parts. From Oromia region Gujii and West Gujii, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem; East and West Wollega, South West, West, East and North Shoa, West and East Hararge zones; Addis Ababa; Harari; Dire Dawa; from South Ethiopia Region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; all zones of Sidama region; from Somali region Dawa, Liben, Afder, Fafan, Sitti, Jarar and Erer zones; from the Central Ethiopia region Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Hadiya, Halaba, Kebena and Tembaro zones; from Southwest Ethiopia Region Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela region Agnuwak, Majang, Nuer and Itang zones; from Benishangul-Gumuz Assosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; from Amhara region West, North and East Gojjam, Awi, Central and South Gondar, North and South Wollo, Waghemra, the Oromo special zone and North Shewa zones; from Tigray region East, Southeast, South and Central zones; and from Afar region Kilbet, Fanti, Hari and Gabi zones. They are expected to receive rainfall amounts ranging from light to moderate (1–29 mm) in many places. Additionally, in Jima Rare, Mida Kagni, Gindabarat, Bako Tibe, Chaliya and Ilu Galan there will be heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. As a result, the expected amount and distribution of this rain will be highly beneficial for seasonal agricultural activities. On the other hand, in Metema, Sherkole, Kumruk, Gambella, Fugnido, Abobo, Kamashi, Gode, Kebridahar, Semera, Elidar, Gewane and Awash Arba the daytime maximum temperatures are forecast to be high, registering between 35 and 40 degrees Celsius, according to our meteorological information.