Daily Weather Report 26 March 21

Weather Summary for previous day

March 20, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተስፋፋ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ቦረና፣ ባሌ፣ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አዲስ አበባ፣ ሐረር፣ድሬዳዋ፤ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም እና ምስራቅ ወለጋ፣ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ኢታንግ ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ ሰሜን፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ፣ምስራቅ ጎጃም እና ምስራቅ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፣ በተጨማሪም በጊዳ አያና፣ ጫዋቃ፣ የትኖራ፣ ደብረ ብርሃን ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ምዕራብ አባያ፣ ጎቤዬሬ፣ ፊቼ እና ፂፂቃ ከ30ሚሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ መንደር 11፣ ፉኝዶ፣ ጫዋቃ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-43.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there was beneficial light rain, and widespread cloud cover was observed in the northwest and western parts of the country. In addition, the following areas received light to moderate rainfall: Jimma, Borena, Bale, Guji and western Guji, western and eastern Hararghe, north, west, southwest and east Shewa, Addis Ababa, Harar, Dire Dawa, Iluababora, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem and eastern Wollega, Agnuwak, Majang, Itang, Sheka, western Omo, Wolayta, Gurage, northern, central and southern Gondar, northern and southern Wollo, Wag Hemra, the special zone of the Oromo people, northern Shewa, eastern Gojjam and eastern Tigray. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm was recorded at Gida Ayana, Chawaka, Yitinora, Debre Birhan, Wolayta Sodo, western Abaya, Gobeyere,Fiche and Tsitsika. On the other hand, Gambella, Mender 11, Fugnido, Chawaka and Gode registered high daytime temperatures ranging from 35 to 43.0°C.

Weather Forecast for next day

March 22, 2026

በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተስፋፋና ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ኖጎብ፣ ዶሎ፣ ሸበሌ፣ አፍዴር፣ ቆራሄ፣ ፋፈን፣ ሲቲ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ ሀሪ እና ጋቢ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በያያ ጉለሌ፣ ግራር ጃርሶ፣ ወራ ጃርሶ፣ገብረ ጉራቻ፣ ሱሉልታ፣ ጫንጮ፣ ውጫሌ፣ ወሊሶ፣ ቶሌ፣ ሰበታ፣ ሰበታ ሀዋስ፣ ሻሸመኔ እና አዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ሸርኮሌ፣ ኩምሩክ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ካማሽ፣ ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ሰመራ እና ኤሊዳር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ።

Tomorrow, rain-producing weather systems will Widespread and heavy cloud cover expected over Mainly Belg benefiting areas and Belg second rainy season areas, also, western and northwestern parts of the country. In line with this , Zones of Oromia Region: Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilu Aba bora, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem; East and West Wollega, South West, West, East and North Shewa; Hara; Dire Dawa; from Southern Ethiopia Region: Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alaba, Kora, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; all zones of Sidama Region; from Somali Region: Dawa, Liban, Nogob, Doolo, Shebelle, Afder, Korahe, Fafan, Sitti, Jarar and Erer zones; from Central Ethiopia Region: Gurage, East Gurage, Maraqo special zone, Silte, Yem special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones; from Southwest Ethiopia Region: Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela Region: Agnuak, Majang, Nuer and Itang zones; from Benishangul Gumuz: Assosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones; from Amhara Region: West, North and East Gojjam, Awi, West, North, Central and South Gondar, North and South Wollo, Waghemra, the Oromo Ethnic Special Zone and North Shewa zones; from Tigray Region: East, South East, South and Central zones; and from Afar Region: Kilbeti, Fanti, Hari and Gabi zones many locations will receive light to moderate rainfall (1–29 mm). In addition, places such as Yaya Gulele, Gerar Jarso, Wera Jarso, Gebre Guracha, Sululta, Chancho, Wuchale, Weliso, Tole, Sebeta, Sebeta Hawas, Shashemene and Addis Ababa may get heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. Such amounts and distribution of rain will be highly beneficial for most agricultural activities. On the other hand, in Metema, Sherkole, Kumruk, Gambella, Fugnido, Abobo, Kamash, Gode, Kebridahar, Semera and Elidar, daytime maximum temperatures are forecast to be high, reaching about 35 to 40 degrees Celsius.