Daily Weather Report 26 March 19
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተስፋፋ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አዲስ አበባ፣ ሐረር፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ ማጃንግ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ፣ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በወራቤ እና ሳህሉ ከ30ሚሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ መንደር 11፣ ማይሃንሳ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ መልካ ጀብዱ፣ ኑራኢራ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-41.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday The northern, northwestern and western parts of the country, which benefited from the belg rains, had widespread cloud cover. In addition, light to moderate rainfall was recorded in Jimma, Borena, Bale and East Bale, Guji and West Guji, West and East Hararge, West, South-West Shewa, Addis Ababa, Harar, Ilubabor, Kelem Wellega, Majang, Sheka, West Gojam, Asosa, Metekel, Gondar, North and South Wello, North Shewa, East and South-East Tigray, while heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Warabe and Sahlu. On the other hand, in Gambella, Village 11, Mayhansa, Semera, Gewane, Awash Arba, Metahara, Melka Jebdu, Nuraira and Gode, the highest daily temperatures were recorded at 35-41.2°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ቆራሄ፣ ፋፈን፣ ሲቲ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ አውሲ፣ ሀሪ እና ጋቢ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በመናሲቡ፣ ቤጊ፣ አይራ፣ ዲዱ፣ ሳለኖኖ፣ ባምባሲ፣ ዳንግላ፣ ጠለምት፣ ቆላ ተምቤን፣ እንደርታ፣ ደሴ ዙሪያ እና ወረኢሉ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ሸርኮሌ፣ ኩምሩክ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ካማሽ፣ ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ።
Tomorrow, rain-bearing weather systems will intensify and continue over the main and second Belg rainfall areas, as well as over the western and northwestern parts of the country. Accordingly, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in many areas of the Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, Southwest, West, East and North Shewa, and East and West Harerge zones of Oromia Region; Addis Ababa; Harari; Dire Dawa; Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo, and Konso zones of South Ethiopia Region; all zones of Sidama Region; Dawa, Liben, Afder, Korahe, Fafen, Siti, Jarar, and Erer zones of Somali Region; Gurage, East Gurage, Mareko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones of Central Ethiopia Region; Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and West Omo zones of Southwest Ethiopia Region; Agnuak, Majang, Nuer, and Itang zones of Gambella Region; Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao Komo zones of Benishangul Gumuz Region; West, North and East Gojjam, Awi, West, North, Central and South Gondar, North and South Wollo, Wag Hemra, Oromo Special Zone, and North Shewa zones of Amhara Region; East, Southeast, South, Central, West and Northwest zones of Tigray Region; and Kilbeti, Fanti, Awsi, Hari, and Gabi zones of Afar Region. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected in areas such as Mana Sibu, Begi, Aira, Didu, Sayo Nono, Bambasi, Dangila, Telemt, Kolla Temben, Enderta, Dessie Zuriya, and Wereilu. Therefore, the expected rainfall amount and distribution will be highly beneficial for Belg season agricultural activities. On the other hand, in Metema, Sherkole, Metekel, Kurmuk, Gambella, Fugnido, Abobo, Gode, Kebridehar, Semera, Elidar, Gewane, and Awash Ariba, the daily maximum temperature is expected to range between 35°C and 40°C