Daily Weather Report 26 March 18

Weather Summary for previous day

March 17, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ቦረና፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ ማጃንግ፣ ሸካ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በአትናጎ፣ ጂንካ እና ኮንሶ ከ30ሚሜ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ መንደር 11፣ ሸርኮሌ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሃንሳ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ፣ መልካ ጀብዱ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-41.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

The areas that benefitted from the belg rains and the western parts of the country had cloud cover yesterday. In addition, light to moderate rainfall was recorded in Jimma, Borena, Bale, Guji and West Guji, West and East Hararge, Ilubabor, Kelem Wellega, Majang, Sheka, North and South Wello and North Shewa; Atnago, Jinka and Konso recorded rainfall of 30 mm. On the other hand, Gambella, Village 11, Sherkole, Addis Zemen, Mayhansa, Semera, Gewane, Awash Arba, Dire Dawa, Melka Jebdu, Kebridehar and Gode recorded the highest temperature of the day at 35-41.2°C.

Weather Forecast for next day

March 19, 2026

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተስፋፋና ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲና አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ጅማ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ቤንችሸኮ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዶሎ፣ ጃራ፣ ፋፈን፣ እና ቆራሔ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦኮሞ እና ካማሺ ዞኖች እና ከአማራ ክልል የምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ዋግኸምራ እና ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆንና፤ በተጨማሪም በጊዳአያና፣ ሆሮ፣ ቢላ ሰዮ፣ ሲቡሲሬ፣ ኢሉገላን፣ አይከል፣ ታች አርማጭሆ፣ ደባርቅ፣ ዳባት፣ ጃናሞራ እና አድርቃይ ላይ ደግሞ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ሸርኮሌ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሃንሳ ፣መተማ፣ ቋራ፣ ሠመራ፣ ጎዴ፣ቀብሪደሃር እና ዶሎኦዶ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ ፡፡

Tomorrow, there will be widespread and strong cloud cover and accumulation over the main and second rainy seasons of the belg, as well as over the western and northwestern parts of our country. In connection with this, the zones of West Arsi and Arsi, Guji and West Guji, Borena, Jimma, West and South West Shewa, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wellega of the Oromia Region; the zones of Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo and South Omo of the Southern Ethiopia Region; the zones of Sidama Region; the zones of Sheka, Kefa, Bench sheko, Konta and West Omo of the Southwestern Ethiopia Region; Dolo, Jara, Fafen, and Korahe zones of Somali Region; Anwak, Itang, and Majang zones of Gambella Region; Metekal, Asosa, Maokomo, and Kamashi zones of Benishangul Gumuz; and East and West Gojam, Awi, North, South, West, and Central Gondar, Waghemra, and North and South Wollo zones of Amhara Region; and West, North-West, Central, East, and South-East zones of Tigray Region will receive light to moderate (1-29mm) rainfall; In addition, Gidayana, Horo, Bila Seyo, Sibusire, Ilugelan, Aykel, Tach Armacho, Debarq, Dabat, Janamora and Adrakay will also experience heavy rainfall of more than 30 mm. On the other hand, in Gambella, Fundo, Asosa, Metekel, Sherkole, Addis Zemen, Mayhansa, Metema, Quara, Samara, Gode, QebriDehar and Doloodo, that the maximum temperature of the day will be recorded as 35 to 40 degrees Celsius.