Daily Weather Report 26 March 17
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በሻምቡ፣ አርጆ፣ ጋምቤላ፣ ቡሬ፣ አቦቦ፣ ፉኝዶ፣ አሺ፣ ተርኮዲ፣ ኩሚ፣ ትንሹ ሜቲ፣ አርባምንጭ፣ ዲላ፣ አጋሮ፣ ዳሮር፣ ዶላአዶ እና አዲስ አለም ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ፉኝዶ፣ ሸርኮሌ፣ ጨዋቃ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሃንሳ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ መተሐራ፣ ኑራኢራ፣ መልካ ጀብዱ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-43.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover in the western and central regions of the country that benefited from the belg rains. In addition, light to moderate rainfall was recorded in Shambu, Arjo, Gambella, Bure, Abobo, Fugendo, Ashi, Tarkodi, Kumi, Tinishu Meti, Arbaminch, Dilla, Agaro, Daror, Dolaado and Addis Alem. On the other hand, in Gambella, Fugendo, Sherkole, Saltuka, Addis Zemen, Mayhansa, Semera, Gewane, Metahara, Nuraira, Melka Jebdu, Kebridehar and Gode, the maximum temperature of the day was recorded at 35-43.0°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲና አርሲ ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ጅማ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ቤንችሸኮ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የመተከል፣ አሶሳ፣ ማኦኮሞ እና ካማሺ ዞኖች እና ከአማራ ክልል የምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር እና ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆንና፤ በተጨማሪም በቡለን፣ ማንዱራ፣ ሸንዲ፣ ኢባንቱ፣ ሻምቡ፣ ሊሙ፣ ማሻ እና በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ደግሞ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ መተማ፣ ቋራ፣ ሠመራ፣ ጎዴ፣ቀብሪደሃር እና ዶሎኦዶ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the main and second rainy seasons of the Belg, as well as over the western and northwestern regions of our country. In this regard, the zones of West Arsi and Arsi, Guji and West Guji, Borena, Jimma, West and Southwest Shewa, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, East and West Wellega from the Oromia Region; the zones of Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo and South Omo from the Southern Ethiopia Region; the zones of Sidama Region; the zones of Sheka, Kefa, Bench Sheko, Konta and West Omo from the Southwestern Ethiopia Region; the zones of Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro from the Central Ethiopia Region; ; The zones of Anwak, Itang and Majang of Gambella region; the zones of Benshangul Gumuz, Metekel, Asosa, Maokomo and Kamashi and the zones of East and West Gojam, North, South, West and Central Gondar and North and South Wollo of Amhara region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall; in addition, Bulen, Mandura, Shendi, Ibantu, Shambu, Limu, Masha and some of their places will receive heavy rainfall of more than 30 mm. On the other hand, our numerical forecast data indicates that the maximum temperature of the day will be recorded as 35 to 40 degrees Celsius in Gambella, Fugendo, Abobo, Asosa, Metekel, Metema, Quara, Samara, Gode, Kebridehar and Doloodo.