Daily Weather Report 26 March 16
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በሰሜን ምዕራብና ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በላይበር፣ ሸንዲ፣ አርጆ፣ በደሌ፣ ጭራ፣ ቴፒ፣ አርባምንጭ እና አንጋጫ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ የነበራቸው ሲሆን፤ በማሻ ከባድ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ፉኝዶ፣ ሸርኮሌ፣ መተማ፣ የጭላ፣ ማይሃንሳ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ መተሐራ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-41.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover in the northwestern and western regions of the country that benefited from the belg rains. Along with this, light to moderate rainfall was recorded in Laiber, Shendi, Arjo, Bedele, Chira, Tepi, Arbaminch and Angacha; heavy rainfall was recorded in Masha. On the other hand, in Gambella, Fugendo, Sherkole, Metema, Yecla, Mayhansa, Semera, Elidar, Gewane, Metahara, Awash Arba, Kebridehar and Gode, the maximum temperature of the day was recorded at 35-41.0°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲና አርሲ ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ቤንችሸኮ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች እና ከአማራ ክልል የምስራቅ ጎጃም እና ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆንና፤ በተጨማሪም የሸካ እና ምዕራብ ኦሞ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ደግሞ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ መተማ፣ ቋራ፣ ሠመራ፣ ጎዴ እና ዶሎኦዶ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the main and second rainy seasons of the belg and over the western parts of our country. In this regard, the West Arsi and Arsi, Guji and West Guji, Borena, Jimma, Ilubabor, Kelem and West Wellega zones of the Oromia region; the Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo and South Omo zones of the Southern Ethiopia region; the Sidama region zones; the Sheka, Kefa, Bench Sheko, Konta and West Omo zones of the Southwestern Ethiopia region; the Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones of the Central Ethiopia region; The Anwak, Itang and Majang zones of Gambella region and the East Gojam and North and South Wollo zones of Amhara region will receive light to moderate (1-29mm) rainfall. In addition, Sheka and West Omo will also experience heavy rainfall of more than 30 mm in some areas. On the other hand, Gambella, Abobo, Asosa, Metekele, Metema, Quara, Samara, Gode and Doloodo will record daily high temperatures of 35 to 40 degrees Celsius.